በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ብሄራዊ ህዝባዊ መርመራ” በሃዋሳ


“ብሄራዊ ህዝባዊ መርመራ” በሃዋሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:09 0:00

“ብሄራዊ ህዝባዊ መርመራ” በሃዋሳ

በደቡብ ክልል “የበዙ” ያላቸው የመብቶች ጥሰቶች መፈፀማቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።

ጥሰቶቹ የሚፈፀሙት ከወሰን እና ከማንነት ጥያቄዎች ጋር በተያያዙ ምክንያቶችና ከህግ ክፍተትና አሠራር ግድፈት የተነሳ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ “ነፃነታቸውን አላግባብና በዘፈቀደ ተነፍገዋል” በሚባል ሰዎች መብቶች ላይ ያተኮረ “ብሄራዊ ህዝባዊ መርመራ” ሃዋሳ ላይ መካሄዱን የሰብዓዊ መብቶች ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ዛሬ ተናግረዋል።

“’ብሔራዊ ምርመራ’ ውስብስብና በሀገርአቀፍ ደረጃ በብዙ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በጥልቀት ለመመርመር፤ ስልታዊና ዘርፈ ብዙ መፍትኄዎችንም ለማፈላለግ የሚጠቅም ዘዴ ነው” ተብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።

XS
SM
MD
LG