በዩናይትድ ስቴትስ እና በተለያዩ የዓለም ሃገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ - ኢትዮጵያ ተወልደው ላደጉባት ድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች የበጎ አድራጎት ሥራን በመሥራት ላይ ናቸው።
የድሬደዋ ልጆችና ወዳጆች ዓለም አቀፍ ማኅበር የተሰኘ መሰባሰቢያ አቋቁመውም ለአቅመ ደካሞችና ትምሕርታቸው መማር ላልቻሉ ተማሪዎች እገዛን ያደርጋሉ። ይህንን ድጋፋቸውን ለማጠናከርም እዚህ ሜሪላንድ ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘውን 39ኛው የኢትዮጵያዊያን የስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ፌስቲቫል አስታከው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በማሰናዳት ላይ ይገኛሉ።
በነገው ምሽትም የእራት ዝግጅት በማሰናዳት የበጎ አድራጎት ተግባራቸውን ለመቀጠል በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የድሬደዋ ልጆች ቀጠሮ ይዘዋል።
/የማኅበሩን እንቅስቃሴ በተመለከተ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/