በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት በወለጋ ያለውን የፀጥታ ኃይሎችን ቁጥር እንዲጨምር ኢሰመኮ ጠየቀ


የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ//ር ዳንኤል በቀለ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ//ር ዳንኤል በቀለ

በምዕራብ ወለጋና ቄለም ወለጋ እየተፈጸመ ያለው ብሔርን መሠረት ያደረገ ግድያ በአስቸኳይ እንዲገታ የጠየቁት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ//ር ዳንኤል በቀለ በዚያ ያለው የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቁጥር በፍጥነት እንዲጨምርም ጥሪ አቅርበዋል።

በኦሮምያ ክልል፣ቄለም ወለጋ ዞን ፣ሃዋ ገላን ወረዳ በሚገኙት መንደር 20 እና 21 በተሰኙ መኖሪያዎች ትናንት ንጹሃንን የገደለው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው የሸኔ ቡድን መሆኑን የአካባቢው ምንጮች መናገራቸውንም ዋና ኮሚሽነርሩ ጠቅሰዋል።

ቡድኑ በዚህ መንገድ የሚቀርቡትን ውንጀላዎች ሲያስተባብል ቆይቷል።

ጥቃቱ በአማራ ክልል ተወላጆች እና ተጠቂዎችን ለመከላከል ሙከራ ባደረጉ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጭምር ያነጣጠረ መሆኑን የገለፁት የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው “የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴው ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።

በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ተጋላጭ ቀበሌዎችን እና መንደሮችን በመለየት አስፈላጊው ጥበቃ እንደሚደረግላቸውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ነዋሪው እራሱን በተደራጀ መልኩ እንዲከላከል የሚሊሻ እና የሕብረተሰብ ፖሊስ ሥርዓት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል ።

/የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሸን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሰጡትን ማብራሪያ የያዘውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:03 0:00

XS
SM
MD
LG