በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፖሊስ በትናንቱ የቺካጎ ጥቃት የተጠረጠረውን ግለሰብ መያዙን አስታወቀ


ሃይ ላንድ ፓርክ ኢሊኖይ
ሃይ ላንድ ፓርክ ኢሊኖይ

ዩናይትድ ስቴትስ ኢሊኖይ ክፍለ ግዛት ቺካጎ ከተማ አቅራቢያ በነበረ ስፍራ የትናንትናው የነጻነት ቀን በዓልን በጎዳና ትርኢት ለማክበርና ለመመልከት ወጥተው በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈጸመ የተኩስ ጥቃት ቢያንስ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 30 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡

የሃይላንድ ፖሊ ኃላፊ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከግድያው ጥቃት ጋር በተያያዘ ፖሊስ ሮበርት ኢ ክሪሞ የተባለውን የ22 ዓመቱን ሰው በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ትናትን ሰኞ ባወጣው መግለጫ በወቅቱ ያልተያዘው ክሪሞ የታጠቀና አደገኛ መሆኑን አስጠንቅቆ ነበር፡፡

የሰኞው ምሽት ጥቃት የተፈጸመው ከቺካጎ ወጣ ብላ በምትገኝ ከተማ በዓሉን በማክበር ላይ በሚገኙት ሰልፈኞች፣ ህጻናት ልጆቻችውን በእጅ መግፊያ ተሽከርካሪ እየገፉ በሚሄዱና ብስክሌት ይነዱ በነበሩ ህጻናት ላይ፣ ከአንድ ህንጻ አናት ሆኖ ቁልቁል በተከፈተ ተኩስ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ተጠርጣሪው ለሰዓታት ተሰውሮ የቆየ መሆኑን የተነገረ ቢሆንም ፖሊስ ክሪሞን እንዴትና በምን ለይቶ እንደያዘው አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

የትናንቱ ጥቃት በትምህር ቤቶች፣ ቤተክስቲያናት ገበያ መደብሮች ላይ የተካሄዱ የሰሞኑ ጥቃቶችን ተከትሎ የተፈጸመ የቅርብ ጊዜ ጥቃት መሆኑ በአሶሼይትድ ፕሬስ ዘገባ ተጠቅሷል፡፡

XS
SM
MD
LG