በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዚምባቡዌ የወርቅ ሳንቲም መሸጥ ጀመረች


የዚምባቡዌ ማዕከላዊ መንግሥት የአገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ያዳከመውን የዋጋ ግሽበት ለመቅረፍ ከዚህ ወር ጀምሮ የወርቅ ሳንቲሞችን መሸጥ እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

አንዱ የወርቅ ሳንቲም ወደ 31 ግራም ያህል እንደሚመዝን ሲነገር በየትኛውም የአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ሊቀየር የሚችል መሆኑን ባኩን አመልክቷል፡፡

ዚምባቡዌ አሁን ያለችበት ሁኔታ ለአራት አስርት ዓመታት ያህል በፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ዘመን ቀውስ ውስጥ ገብቶ የነበረውን የምጣኔ ሀብት መጥፎ ትዝታ እንደሚቀሰቅስ ተነግሯል፡፡

በዚምባቡዌ ዓመታዊ የግሽበት መጠኑ በሰኔ ወር ውስጥ 192 ከመቶ መድረሱ ተገልጿል፡፡

በዚምባቡዌ አዲስ የብር ኖት እኤአ በ2019 የወጣ ቢሆንም ዋጋውን ያጣው ወዲያኑ እንደነበር የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG