በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በድምበር ከተማዋ በደረሰ ፍንዳታ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀች


ጁላይ 2፣ 2022 ዓ.ም - በዩክሬን ካርኪቭ አቅራቢያ አንድ ወታደር የውጊያ ይዞታውን ሲቀይር 
ጁላይ 2፣ 2022 ዓ.ም - በዩክሬን ካርኪቭ አቅራቢያ አንድ ወታደር የውጊያ ይዞታውን ሲቀይር 

ከዩክሬን ጋር በድንበር በምትገናኝ አንድ የሩሲያ ከተማ ላይ ዛሬ የደረሰ ፍንዳታ ሶስት ሰዎች መግደሉት የሩሲያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ቤልግራድ በተሰኘው ከተማ የደረሰው ፍንዳታ በደርዘን የሚቆጠሩ የመኖሪያ ህንፃዎች ላይ ጉዳት ማድረሱም የተገለፀ ሲሆን የሩሲያ ህግ አውጪ የሆኑት አንድሬ ክሊሻስ ለፍንዳታው ወታደራዊ ምላሽ እንዲኖር ጠይቀዋል።

የዩክሬን ባለስልጣናት በሩሲያ ላይ ስለደረሰው ጥቃት ብዙም የተናገሩት ባይኖርም በሩሲያ ቁጥጥር ስር የሆነችው ሜሊቶፖል ከንቲባ ኢቫን ፌድሮቭ በቴሌግራም ባስተላለፉት መልዕክት ዩክሬን ከአራቱ የሩሲያ ወታደራዊ ሰፈር አንዱን መምታቷን ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዩክሬን ምስራቃዊ ዶንባስ ክፍለግዛት በተካሄደ ውጊያ ሩሲያ ሊሲቻንስክ ከተማ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅማለች። በሩሲያ የሚደገፉት የዩክሬን ተገንጣዮችም ከተማዋን መክበባቸውን ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG