በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ ቀንድ የተባባሰው ረሃብ የጤና ቀውስ ፈጥሯል


በድርቅ በተጠቃው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አንዲስ ሴት በአህያ ውሃ ጭና ስትወስድ - ፎቶ ሮይተርስ
በድርቅ በተጠቃው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አንዲስ ሴት በአህያ ውሃ ጭና ስትወስድ - ፎቶ ሮይተርስ

በአፍሪካ ቀንድ እየተባባሰ የሄደው አጣዳፊ ረሃብ ከፍተኛ የጤና አደጋ እየደቀነ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል።

የጤና ተቋሙ የአፍሪካ ቀንድ የአደጋ ግዜ ሀላፊ የሆኑት ሶፊ ሜስ እንደተናገሩት በቀጠናው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ለህመም እና ሞት እየዳረገ የሚገኘውን ረሃብ እና የጤና ቀውስ ለማርገብ አስቸኳይ ርምጃ ያስፈልጋል። አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት ለዚህ የሚውል 16.5 ሚሊየን ዶላር ከአስቸኳይ ጊዜ ፈንዱ መልቀቁን ሜስ ጠቁመዋል።

በአፍሪካ ቀንድ እየተባባሰ በሄደው ድርቅ ምክንያት 20 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ያስታወቀ ሲሆን ሰዎች ምግብ እንዲያገኙ ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ እና የጤና አገልግሎትም ችላ ሊባል እንደማይገባ ሜስ ገልፀዋል።

ሜስ ጨምረው የንፁህ ውሃ እጥረት ለበሽታዎች መከሰት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የገለፁ ሲሆን ድርቁ የውሃ ምንጮችን ማድረቁን፣ ሰዎች ምግብ፣ ውሃ እና ለከብቶቻቸው ምግብ ፍለጋ እንዲሰደዱ ማድረጉን በዚህም ምክንያት የሰዎች የአኗኗር ሁኔታ እያሽቆለቆለ መሄዱን አብራርተዋል።

XS
SM
MD
LG