የመንግስት ግልበጣ በተጋሄደባቸው ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ እና ጊኒ የጠፋውን የፖለቲካ ስምምነት ለመፍታት የሚጥረው የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) አባላት የሆኑ የአፍሪካ መሪዎች ዛሬ ጉባኤ አካሂደዋል።
ኤኮዋስ ባለፈው ወር ባካሄደው ጉባኤ መንግስት በሶስቱ ሀገራት ላይ የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ማዕቀብ የጣለ ሲሆን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እስኪያካሂዱ ድረስ ከቀጠናው ቡድን አባልነትም በጊዜያዊነት ታግደዋል።
የማሊ ባለስልጣናት እ.አ.አ በየካቲት 2024 ምርጫ ለማካሄድ እና በመጋቢት 2023 ደግሞ በህገመንግስቱ ላይ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ የሚያስችላቸውን ዕቅድ በቅርቡ አስታውቀዋል። ዛሬ በጋና ዋና ከተማ የተጀመረው ጉባኤ ዕቅዱን ይቀበል አይቀበል እንደሆን እየተጠበቀ ነው።
ኤኮዋስ በጥር ወር ላይ በወሰነው ውሳኔ ማሊ ከቡድኑ አባላት ጋር ያላትን ማንኛውንም የንግድ ግንኙነት በማገዱ የማሊን ኢኮኖሚ ክፉኛ ጎድቶታል።
ጊኒ እና ቡርኪናፋሶን የተቆጣጠሩት ወታደራዊ ቡድኖች ለሶስት አመት በሽግግር መንግስት ለማስተዳደር ያቀረቡትን ጥያቄ ግን፣ ምርጫ ለማካሄድ ረጅም ጊዜ ያስጠብቃል በማለት ውድቅ አድርገውታል።