በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳን ውስጥ በተቃውሞ ሰልፍ ላይ ሰባት ሰዎች ተገደሉ


ትናንት ሀሙስ ሱዳን ውስጥ በተካሄዱ የተቃውሞ ሠልፍ፤ ካርቱም፣ ሱዳን
ትናንት ሀሙስ ሱዳን ውስጥ በተካሄዱ የተቃውሞ ሠልፍ፤ ካርቱም፣ ሱዳን

ትናንት ሀሙስ ሱዳን ውስጥ በተካሄዱ የተቃውሞ ሠልፎች ላይ ሰባት ሰዎች በጥይት መገደላቸውን የህክምና ሠራተኞች ገለጡ። በዋና ከተማዋ በካርቱም እና በሌሎችም ከተሞች ሰልፍ የተካሄደው የቀድሞው አምባገነን መሪ ኦመር አል በሽርን ከሥልጣን ያስወገደውን እና የሥልጣን ክፍፍል አስተዳደር እንዲመሰረት ያደረገውን ህዝባዊ አመጽ ሦስተኛ ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ መሆኑ ተዘግቧል።

ትናንት የሱዳን ብዛት ያለው የፀጥታ ኃይል ያሰማራ እና የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያቋረጠ ቢሆንም ብዛት ያለው ህዝብ ጎዳና ላይ ወጥቶ ከስምንት ወራት በፊት አስተዳደሩን በጨበጠው ወታደራዊ መንግሥት ላይ ተቃውሞ አሰምቷል።

ትናንት ከተገደሉት ሰባት ሰዎች ውስጥ አምስቱ ኡምዱርማን ሲሆን አንድ ሰው ካርቱም እንዲሁም አንድ ልጅ ባህሪ ከተማ ውስጥ መገደላቸው ተመልክቷል። በዚህም ከመፈንቅለ መንግሥቱ ወዲህ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 110 መድረሱ ታውቋል። ከሱዳን መንግሥት ባለሥልጣናት በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም።

የተመድ የሱዳን ልዩ ልዑክ ቮልከር ፐርዝ የመንግሥቱ ባለሥልጣናት የህዝቡን በሰላማዊ መንገድ የመሰባሰብ መብት እንዲያከብሩ ባለፈው ሳምንት ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG