በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ውስጥ እያሻቀበ ነው


ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ውስጥ እያሻቀበ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:16 0:00

ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ውስጥ እያሻቀበ ነው

በኮቪድ-19 ምክንያት በጠና ታምመው የከፍተኛ ህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ያሉ ሰዎች ቁጥር ባለፉት ሦስት ሣምንታት ውስጥ ከ36 ወደ 70 መሻቀቡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ።

የሰዉ መዘናጋትና ቫይረሱ ጠፍቷል በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ምክንያት አለመጠንቀቅ ለኮሮናቫይረስ ሥርጭት በእጥፍ ማሻቀብ ምክንያት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የኮሮናቫይረስ መዛመት ላለፉት ወራት ቀንሶ እንደነበረና ከስድስት ሣምንታት ወዲህ ግን በኮቪድ-19 የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

በተለይ ከሦስት ሣምንታት ወዲህ ለቫይረሱ የሚጋለጠው ሰው ቁጥር ማሻቀቡንና በፅኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥርም በእጥፍ መጨመሩን የሚኒስቴሩ የኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ ተናግረዋል ።

XS
SM
MD
LG