በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰላም ድርድር ጉዳይ የተቃዋሚዎች ጥሪና የመንግሥት ምላሽ


በሰላም ድርድር ጉዳይ የተቃዋሚዎች ጥሪና የመንግሥት ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:33 0:00

በሰላም ድርድር ጉዳይ የተቃዋሚዎች ጥሪና የመንግሥት ምላሽ

በኢትዮጵያ “ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት መንግሥት ሁሉን አቀፍ ድርድር ማካሄድ አለበት” ሲሉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ጠይቀዋል።

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች አገልግሎት ሚኒስትሩ ዴ’ኤት አቶ ከበደ ዴሲሳ ደግሞ “ከህወሓት ጋር የሚደረገው ድርድር በቂ ነው፤ ‘ሸኔ’ ሲሉ የጠሩትን ቡድን ጨምሮ ሌሎች ታጣቂዎች ተላላኪ ናቸው” ብለዋል።

በሌላ በኩል “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው” ብለዋል የቡድኑ ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ መሆናቸውን የሚናሩት አቶ ኦዳ ተርቢ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል።

ሰሞኑን ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በመቶዎች በሚቆጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጅ በሆኑ ነዋሪዎች ላይ ለተፈፀመው ጥቃትና ዘር ተኮር ግድያ ባለሥልጣናቱ ተጠያቂ በሚያደርጉትና ሸኔ በሚሉት፤ ሆኖም “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” እንደሚባል በሚናገረውና ውንጀላውን በሚያስተባብለው ቡድን ላይ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን መንግሥት አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG