በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደራሼ ምክንያት ባለሥልጣናትና ሌሎችም ታሠሩ


በደቡብ ክልል ደራሼ
በደቡብ ክልል ደራሼ

በደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ ውስጥ ለህይወት መጥፋትና ለንብረት ውድመት ምክንያት በሆነ በቅርቡ የተፈጠረ ሁከት ጠርጥሬአቸዋለሁ ብሎ በያዛቸው 300 ሰዎች ላይ የከፈተውን ምርመራ ማጠናቀቁን የክልሉ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።

መደበኛ እንቅስቅሴ እያደረጉ መሆናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ የተናገሩ ነዋሪዎች አሁንም ቢሆን አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ አመልክተዋል።

ልዩ ወረዳውን በዞን ለማደራጀት ከሚቀርበው ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳ ሁከትና በተፈፀመ ጥቃት 72 የፌዴራል ፖሊስና የክልል ልዩ ኃይል አባላትና አራት ባለሥልጣናት መገደላቸውን ቢሮው ለቪኦኤ ገልፆ በምርመራው የደረሰበት ደረጃ ክሥ ለመመሥረት እንደሚያስችለው ጠቁሟል።

/ዝርዝሩን ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:23 0:00

XS
SM
MD
LG