በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደም እንደጎርፍ ያፈሰሰ እልቂት - የዐይን እማኞች ማንነትን መሰረት ስላደረገው ጥቃት ይናገራሉ


በአፍሪካ በሕዝቧ ቁጥር ከፍተኛነት ሁለተኛዋ በሆነችው ኢትዮጵያ ሲካሄዱ በቆዩት በማንነት ላይ የተነጣጠሩ ጥቃቶች በአንዲት መንደር እና አካባቢዋ በተፈጸመ ጭፍጭፋ በቅርቡ በመቶዎች የተቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ተገድለዋል” ሲል አሶሽዬትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘገበ።

በዚህም “ኢትዮጵያውያን የፌዴራል መንግሥቱ ለምን ዜጎቹን ከዚህን መሰል ዘውግ ተኮር ግጭቶች መከላከል ተሳነው” ሲሉ ግራ እንደተጋቡ ነው ብሏል .. አሶሽዬትድ ፕሬስ በዘገባው። ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች የአካባቢውን ባለሥልጣናት ካስጠነቀቁ በኋላም “ደም እንደ ጎርፍ መፋሰሱ ግን አልቀሩም” ማለታቸውንም ዘግቧል።

ነዋሪዎቿ በቅርቡ በመንግሥት ኃይሎች እና በአማጽያኑ መካከል የተካሄዱ ውጊያዎች በፈጠሩት አደገኛ ሁኔታ ምክንያት ሥጋት ውስጥ በሰነበቱባት አንዲት በኦሮምያ ክልል ውስጥ የምትገኝ አነስተኛ የገጠር መንደር በእጅጉ የታጠቁ ሰዎች መታየታቸውን አሶስዬትድ ፕሬስ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

“እኛን እንደማይነኩን ያረጋገጡልን ታጣቂዎች፤ ከኛ ጋር ጉዳይ እንደሌላቸው ነገሩን።” ሲሉ ኑር ሁሴን አብዲ የተባሉ አንድ የመንደሪቱ ነዋሪ ለአሶሼትድ ፕሬስ በሰጡት አስተያየት የገጠማቸውን ሲያስረዱ

“በተጨባጭ የሆነው ግን ለእልቂት የዳረገ ድርጊት ነው። መንደራችንን በሙሉ ከበቡ። ከዚያ የተከተለው የደም ጎርፍ ነው።” ብለዋል

በከፍተኛ ሥጋት እንደተዋጡ ከመኖሪያ ቤታቸው ጣሪያ ላይ ተሸሽገው ሰኔ አስር ቶሌ በተባለችው የገጠር መንደር እና አካባቢዋ ከደረሰው ግድያ የተረፉት አቶ አብዲ በኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከተፈጸሙት የከፉ የጅምላ ግድያዎች የአንዱ የዓይን ምስክር ለመሆን በቅተዋል።

ጥቃቱ በአፍሪካ በሕዝቧ ቁጥር ከፍተኛነት ሁለተኛዋ በሆነችው ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከደረሱት በማንነት ላይ የተነጣጠሩ ጥቃቶች የአማራ ተወላጆች የበዙበት፤ በአጠቃላይም በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች የተጨፈጨፉበት ነው።

ከጅምላ መቃብር የተጣሉ ቁጥራቸው የበዙትን ጨምሮ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን አስከሬኖች አሁንም እያገኙ መሆናቸውን በርካታ የዓይን ምስክሮች ለአሶሽዬትድ ፕሬስ ገልጠዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የአማራ ማህበር በበኩሉ በጥቃቶቹ 503 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን አመልክቷል። የሟቾችን ቁጥር የሚያመለክቱትን አሃዞች ግን የመንግስት ባለስልጣናት ግን ይፋ አላደረጉም።

መሃመድ ከማል የተባሉ አንድ እማኝ ሲናገሩ ቁጥራቸው 430 የሚደርሱ ሟቾች አስከሬን ቀብር መፈጸሙን እና የተቀሩት ሟቾች አስከሬን ግን አሁንም በወደቁበት በመበስበስ ላይ ናቸው ብለዋል።

ታጣቂዎቹ እንመለሳለን ብለው መዛታቸውን የጠቀሱት አቶ መሃመድ አክለውም በሕይወት የተረፉትን ወደ ሌላ አካባቢ ወስዶ እንዲያሰፍራቸው የኢትዮጵያን መንግስት ተማጽነዋል።

"ጨቅላ ህፃናትን፣ ልጆችን፤ ሴቶችና አዛውንቶችን ገድለዋል።” ያሉት ደግሞ አህመድ ቃሲም የተባሉ የመንደሪቱ ነዋሪ ናቸው። በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የአማራ ማህበር በበኩሉ እንዳስታወቀው ከሟቾቹ መካከል የአንድ መቶ ዓመት ዕድሜ ባለ ጸጋ አዛውንት እና የአንድ ወር ህጻን ሲገኙበት፤ አንዳንድ ሰዎች የተገደሉት ለመደበቅ ራሳቸውን ለማትረፍ ከተጠለሉበት መስጊድ ውስጥ ሳሉ ነው።

ነዋሪዎች እና የክልሉ መንግሥት ባለ ሥልጣናት የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀውን ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራውን ቡድን ተጠያቂ አድርገዋል።

የቡድኑ ቃል አቀባይ በበኩላቸው “የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ‘ይደግፋሉ’ በሚል በሚጠረጥሯቸው የመንደሩ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት የከፈቱት ከቡድኑ ጥቃት በማፈግፈግ ላይ የነበሩ የፌደራል መንግስት ወታደሮች እና የክልሉ ታጣቂዎች ናቸው።” ሲሉ ውንጀላውን አስተባብለዋል።

“ኢትዮጵያውያን የፌዴራል መንግሥቱ እንደምን ዳግም ዜጎቹን ከዚህን መሰል ዘውግ ተኮር ግጭቶች መከላከል ተሳነው” ሲሉ ግራ መጋባታቸውን ጠቅሶ “ዘውግን መሠረት ያደረገው ፌድራላዊ ሥርዓት ዳህጣን ማኅበረሰቦችን ለምን የጥቃት ተጋላጭ አደረገ” ሲሉ መጠየቃቸውን AP በዘገባው አውስቷል።

አሶሴትድ ፕሬስ አክሎ ታዋቂው ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በተለይ ባለፉት አራት ዓመታት እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ያንጸባረቀባቸውን እና በእነኚህ ጥቃቶች ህይወታቸውን ላጡ ሰላማዊ ዜጎች መታሰቢያ ያደረጋቸውን ሁለት ዜማዎች መልቀቁን ዘግቧል።

ከዘፈን ግጥሞቹም በአንዱ "የሞት ተራራ ከፊቴ ሲመጣ ዝም ማለት በጭራሽ አማራጭ አይደለም" ማለቱን ጠቅሷል።

ባለፈው አርብ ዕለት በጎረቤት አማራ ክልል በሺዎች የተቆጠሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግድያዎቹን በመቃወም ፍትህ የጠቁበት ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበኩላቸው የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎቹ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመራቸውን ቢናገሩም ከአሁን ቀደም በተከታታይ የደረሱትን ጥቃቶች በማስታወስ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተፈጽሞ ማየት መርጠዋል ብሏል።

የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባለፈው ሃሙስ በሰጡት አስተያየት በሁሉም ቦታዎች የጸጥታ ጥበቃ እንዲረጋገጥ ማድረግ አዳጋች መሆኑን አምነው፤ እየተወሰደ ያለው እርምጃ “የጠላትን ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ አቅም የሚያሽመደምድ ይሆናል።” ብለዋል።

የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች በቁጥራቸው በኢትዮጵያ ሁለተኛው ትልቁ ቢሆኑም በአንዳንድ አካባቢዎች በአነስተኛ ቁጥር መገኘታቸው ለጥቃት ኢላማ እንዳጋለጣቸው የጠቀሰው ዘገባ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮምያ ክልሎች ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች ብቻ በርካታ ሰዎች መገድላቸውንም አስታውሷል።

ሙሉቀን ተስፋው የተባለ በአማራ ላይ የሚደርሰውን በደሎች የሚከታተል የማኅበረሰብ ተሟጋች በበኩሉ "ከክልላቸው ውጪ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ህጋዊ እና ፖለቲካዊ ውክልና ስለሌላቸው ከለላ አይሰጣቸውም” ሲል ለአሶስዬትድ ፕሬስ ተናግሯል።

“አማርኛ ተናጋሪዎችን ለመቀነስ የሚጥሩ የኦሮምያ ክልል የመንግሥት ባለሥልጣናት ንግግሮችም ነበሩ።" ሲልም አቶ ሙልቀን ከሷል።

የተቃዋሚው ‘ናማ’ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ በለጠ ሞላ በበኩላቸው “ጸረ-አማራ ትርክት ከ50 ዓመታት በላይ እየተሰራጨ ቆይቷል” ማለታቸውን ያወሳው አሶስዬትድ ፕሬስ

“በኦሮምያና በቤኒሻንጉል የሚኖሩ አማሮች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው።

አንዳንድ የኦሮምያ ክልል ገዥ ፓርቲ አባላትም “ከሸማቂው ቡድን ጋር ይሰራሉ ወይም ይደግፉታል” ሲሉ መክሰሳቸውን አሶሽዬትድ ፕሬስ ጨምሮ ዘግቧል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:51 0:00

XS
SM
MD
LG