ዓለም እጅግ ተቸግሮ ካለበት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳይወጣ አንድ ሌላ ወረርሽኝ ቀድሞ ተደብቆ ከነበረበት አፍሪካ ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች በፍጥነት በመሰራጨት ላይ ይገኛል።
በሽታው እየተሰራጨ ያለበት ፍጥነትና እያካለለ ያለው የዓለም ክፍል ብዛት የዓለም የጤና ድርጅትንና የተላላፊ በሽታ ባለሙያዎችን አያሳሰበ ይገኛል።
Monkeypox - የዝንጀሮ ፈንጣጣ ይባላል።
እንግዱ ወልዴ የበሽታውን ምንነትና አሁን ያለበትን የስርጭት ደርጃ የሚመለከት አጭር ዝግጅት ይዟል።