በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን ዩክሬን ላይ ጦርነት ካስጀመሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ሀገር ጉብኝት ሊያደርጉ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የኢሊዩሺን ኢል-96-300 አውሮፕላን ቭላድሚር ፑቲን አሳፍሮ ፊንላንድ በሚገኘው ሄልሲንኪ ቫንታ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ እአአ ነሐሴ 21/2019
ፎቶ ፋይል፦ የኢሊዩሺን ኢል-96-300 አውሮፕላን ቭላድሚር ፑቲን አሳፍሮ ፊንላንድ በሚገኘው ሄልሲንኪ ቫንታ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ እአአ ነሐሴ 21/2019

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በዚህ ሳምንት በማዕከላዊ እስያ የሚገኙ የቀድሞ የሶቪየት ህብረት ክፍለ ግዛት የነበሩ ሁለት ሀገሮችን እንደሚጎበኙ የመንግሥቱ ቴሌቭዥን ዘገበ።

ዩክሬን ላይ ጦርነት እንዲከፈት ካወጁ ወዲህ ይህ የመጀመሪያ የሚታወቅ የውጭ ጉዞ እንደሚሆን ተገልጿል።

ፑቲን ትናንሾቹን የቀድሞ የሶቪየት ክፍላተ ሀገር ታጂኪስታንን እና ቱርክሜንስታንን ከጎበኙ በኋላ ወደ ሞስኮ ተመልሰው የኢንዶኒዥያ ፕሬዚዳንት ጆኮ ዊዶዶን ተቀብለው እንደሚያነጋግሩ የመንግሥቱ ቴሌቭዥን ዘግቧል።

ፑቲን ባለፈው የካቲት መጀመሪያ በቻይና ካደረጉት ጉብኝት ወዲህ ከሀገር ውጭ የሚታወቅ ጉብኝት አድርገው አያውቁም።

XS
SM
MD
LG