በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ላይ ጥቃት አደረሰች


ሩሲያ በኪየቭ ላይ የፈጸመችው የቦምብ ድብደባ
ሩሲያ በኪየቭ ላይ የፈጸመችው የቦምብ ድብደባ

ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ላይ በዛሬው ዕለት ጥቃት አድርሳለች። የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ኪልትሽኮ በዚህ የቦንብ ጥቃት በትንሹ አንድ የመኖሪያ አፓርትማ ተመትቷል ብለዋል።

ጥቃቱ የቡድን ሰባት ሃገራት እና ባለጸጋዎቹ ሃገራት በጀርመን በተሰበሰቡበት በተመሳሳይ ዕለት ነው የተፈጸመው። አባል ሃገራቱ በዛሬው ውይይታቸው የሩሲያ ዩክሬንን መውረር ዐብይ ትኩረታቸው ነው። የዩክሬን ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ ትላንት ቅዳሜ በዚህ የመሪዎች ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ከመሪዎቹ ስብሰባ መጀመር በፊት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ሃገራቸው እና ሌሎች የቡድን ሰባት አባል ሃገራት በሩሲያ ላይ የምጣኔ ሃብት ጫና ለማሳደር ከሩሲያ ወርቅ መግዛትን እንደሚያግዱ አስታውቀዋል።

ይህ የሩሲያ ጥቃት በኪየቭ ላይ የተፈጸመው የዩክሬን ወታደሮች የሃገሪቱን ምስራቃዊ ክፍል ሲየቬሮዶኔትስክን ለቀው በወጡ በማግስቱ ነው። ይህ ለሩሲያዊያን ሳምንታት ከቆየ ከታላቅ ጦርነት በኋላ የተመዘገበ ድል ሲሆን የዓለም አቀፍ የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ ግሽበትን የሚያስከትል ነው።

በተመሳሳይ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የሚያርፍ ሮኬት ጥቃት አስጀምራለች። ጥቃቶቹም ከቤላሩስ የአየር ክልል መነሳታቸው የተመዘገበ ሲሆን ይህም ብላድሚር ፑቲን ከቤላሩሱ አቻቸው ፕሬዘዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ከመገናኘታቸው ከሰዓት በፊት ተፈጽሟል።

XS
SM
MD
LG