የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የ 2020 የምርጫ ውጤትን እንዲሽሩ የሀገሪቱ የፍትህ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ሃላፊዎች ላይ ጫና ያሳድሩ ነበር ሲሉ በካፒቶል ላይ ጥር 6 ቀን የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ምርመራ የሚያካሂዱት የኮሚቴ አባላት በዝርዝር ይፋ አደረጉ።
የኮሚቴውን አምስተኛ ቀን ውሎ የተከታተለችው የቪኦኤዋ የም/ቤት ጉዳዮች ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን እንደላከችው ሪፖርት ከሆነ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን የሃሰት ክስ አንዳንድ የሪፐብሊካን ምክር ቤት አባላትም ሲገፉበት ቆይተው በኋላ ግን አዲሱን ፕሬዚዳንት ጆባይደንና ነጩን ቤተ መንግሥት ምህረት ጠይቀዋል።