በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት የእርዳታ አውሮፕላኖች መቀሌ እንዳያርፉ መከልከሉን መንግሥት ገለፀ


ፎቶ ፋይል መቀሌ ከተማ
ፎቶ ፋይል መቀሌ ከተማ

- የትግራይ ክልል መንግሥት ክሱን አስተባብሏል

የእርዳታ አውሮፕላኖች መቀሌ ኤርፖርት እንዳያርፉ መከልከሉን የኢትዮጵያ መንግሥት ሲገልጽ፣ የትግራይ ክልል መንግሥት በበኩሉ ክሱን አስተባብሏል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፤ መንግሥት ህወሓት እገዳ ማድረጉን ያረጋገጠው ከለጋሽ ድርጅቶች መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ህወሓት በዛሬው መግለጫ የእርዳታ አውሮፕላኖች መቀሌ እንዳያርፉ አግዷል መባሉን ቢያስተባብልም፣

“አውሮፕላን ማረፊያው ግን በነዳጅ እጥረት ምክንያት ሥራ አቁሟል” ብሏል፡፡ በነዳጅ እጥረት ምክንያት ይህ ሊከሰት እንደሚችል ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢዎች ሲያሳውቅ መቆየቱን ገልጿል።

ወደ ክልሉ በቂ ነዳጅ በመግባት ላይ መሆኑን የገለጹት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደሕንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ጋር ባደረጉት ውይይት ይህን ክስ ማስተባበላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG