በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከማራዶና ሞት ጋር በተያያዘ በአርጀንቲና 8 የህክምና ባለሙያዎች ተከሰሱ


ፎቶ ፋይል፦ ታዋቂው የአርጀቲና እግር ኳስ ተጫዋች ዲያጎ ማራዶና
ፎቶ ፋይል፦ ታዋቂው የአርጀቲና እግር ኳስ ተጫዋች ዲያጎ ማራዶና

እኤአ በ2020 የቀዶ ጥገና ህክምና ከተደረገለት ሁለት ሳምንት በኋላ ያገግምበት በነበረው አልጋ ላይ ከሞተው ታዋቂው የአርጀቲና እግር ኳስ ተጫዋች ዲያጎ ማራዶና ሞት ጋር በተያያዘ 8 የህክምና ባለሙያዎች በቸልተኝነት ወንጀል እንደሚከሰሱ ተነገረ፡፡

አንድ የፍርድ ቤት ዳኛ ትናንት ረቡዕ ባስተላለፉት ትዕዛዝ የማራዶናን ቤተሰብ ሀኪምና ነርሶችን ጨምሮ 8ቱ የህክምና ባለሙያዎች በቀረበው ማስረጃ መሰረት ማራዶና “እንዳይሞት ማድረግ የሚያስችላቸውን” እርምጃ መውስደ ባለመቻላቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ መወሰናቸው ተሰምቷል፡፡

አልኮልና አደገኛ ዕጾች ባስከተሉበት የጤና መታወክ ሲሰቃይ የነበረው ማራዶና፣ በ60 ዓመቱ ህይወቱ ያለፈው፣ በደም መርጋት ምክንያት ከተደረገለት የአንጎል ቀዶ ጥገና ሲያገግም በነበረበት ወቅት ደርሶበታል በተባለው የልብ ድካም መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ወደ 20 የሚጠጉ የህክምና ባለሙያዎች ቡድን ባላፈው ዓመት በደረሱበት ድምዳሜ ለማራዶና ይደረጉ የነበሩ የህክምና አገልግሎቶች “ግድፈትና ወጥነት የጎዳለቸው” እንደነበሩ መስክረዋል፡፡

ተከሳሾቹ በሙሉ ተጠያቂ አለመሆናቸውን ያስታወቁ ሲሆን ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከ8 እስከ 25 ዓመት ሊደርስ በሚችል እስር ሊያስቀጣቸው እንደሚችልም የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG