በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዚምባቡዌ ሐኪሞችና መምህራን በዶላር እንዲከፈላቸው ጠየቁ


በዚምባቡዌ ሐኪሞች ተቃውሞ ሰልፍ
በዚምባቡዌ ሐኪሞች ተቃውሞ ሰልፍ

የዚምባቡዌ መምህራን ማህበራት ደመወዛችን ዋጋው እያሽቆለቆለ በመጣው የዚምባቡዌ ገንዘብ ሳይሆን በአሜሪካን ዶላር ይከፈለን በማለት አድማ የመቱትን የአገሪቱን የጤና ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡

ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በዚምባቡዌ የመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ የሚሰሩ ዶክተሮችና ነርሶች መንግሥት ደመወዛቸውን ተመልክቶ እንዲያሻሽል በመጠየቅ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

የአንዳንዶቹ ደመወዝ በወር ከ25 ዶላር ያነሰ መሆኑ ሲገለጽ፣ የአብዛኞቹ የወር ደመወዝ ሲመነዘር ወደ 55 ዶላር የሚጠጋ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ይህም ድሮ ያገኙት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በአስር እጅ መቀነሱን ሠራተኞቹ ሀራሬ ለሚገኘው የአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG