በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰማዕታት ዕለት በትግራይ


መቀሌ
መቀሌ

በትግራይ የሰማዕታት ዕለት ለ34ኛ ግዜ ዛሬ ታስቦ መዋሉን ክልሉን እያስተዳደሩ ያሉት ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

መቀሌ ላይ ዛሬ የወጣው መግለጫ ዕለቱ ከ34 ዓመት በፊት በዚሁ ዕለት ሃውዜን ገበያ ላይ በተፈፀመ የአየር ድብደባ የተገደሉ፣ የሃገሪቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም የነበሩትና ከሦስት ዓመት በፊት የተገደሉት ጄኔራል ሰዓረ መኮንና አብረዋቸው የተገደሉት ሜጄር ጄነራል ገዛኢ አበራ፣ እንዲሁም “ከአንድ ዓመት በፊት በዚሁ ዕለት በቶጎጋ ለገበያ በተሰበሰበ ህዝብ ላይ ተፈፅሟል” ሲል በጠቆመው የአየር ድብደባ ለተገደሉና “ባለፉት 47 ዓመታት ውስጥ ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ መብቶች መከበርና ሰላም መስዋዕት የከፈሉ የሚታሰቡበት መሆኑን አመልክቷል።

ዕለቱ ሻማ በማብራት፣ የጥበብ ሥራዎችን በማቅረብና ውይይቶችን በማካሄድ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ታስቦ መዋሉን ሪፖርተራችን ሙሉጌታ አፅብሃ ከመቀሌ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG