በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ ከተማ የተፈፀመው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ኦፌኮ ጠየቀ


በጋምቤላ ከተማ የተፈፀመው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ኦፌኮ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:00 0:00

በጋምቤላ ከተማ የተፈፀመው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ኦፌኮ ጠየቀ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በቅርቡ በጋምቤላ ከተማ በንጹሃን ዜጎችላይ ተፈፀመ ያለው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል።

በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን እየተዘዋወረ ያለው በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እንደተፈፀመ የሚያሳየው ግድያ እንዲጣራ እና ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስቧል።

የጋምቤላ ክልል መንግሥት ክልሉን ከታጣቂዎች ለመከላከል ተካሄደ ባሉት ጦርነት መሰል የተኩስ ልውውጥ 17 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የጋምቤላን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡና በተወሰዱ እርምጃዎች ላይ ማጣራት እንዲያደረግ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል በነቀምቴ ከተማ ባለፈው ሳምንት ውስጥ አንድ ወጣት በጸጥታ ኃይሎች መገደሉን ከሟች ቤተሰቦች መካከል ገልጸዋል።

በዚህ ዙሪያ ከከተማውም ሆነ ኦሮምያ ክልል ባለሥልጣናት ለማጣራት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG