በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ኮሪያ የራሷን መንኩራኩር ተጠቅማ ሳታላይት ወደ ሕዋ አመጠቀች


ፎቶ ፋይል፦ ስለ ፈንጂዎች የሚያስጠነቅቅ ዓለምአቀፍ ምልክት
ፎቶ ፋይል፦ ስለ ፈንጂዎች የሚያስጠነቅቅ ዓለምአቀፍ ምልክት

ደቡብ ኮሪያ አገር ውስጥ በተሰራ የጠፈር መንኮራኩር ተጠቅማ ሳተላይት ወደ ምህዋር ለማምጠቅ ያደረገችው ሁለተኛ ሙከራ መሳካቱን ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ። ይህም ደቡብ ኮሪያ በጠፈር እንቅስቃሴው ራሷን የቻለች አገር ለመሆን ለአላት ትልቅ እቅድ ቁልፍ እርምጃ ተደርጎ ታይቷል።

"ኑሪ" የተሰኘው ባለ ሦስት እርከን መንኩራኩር በደቡብ ምዕራብ ጎሄንግ ጠረፍ አካባቢ ካለች ትንሽ ደሴት ከሚገኘው የጠፈር ማዕከሏ ከመጠቀ በኋላ በርካታ ሳተላይቶችን ወደ ምህዋር አሰማርታለች” ሲሉ የጠፈር ሚኒስትሯ ሊ ጆንግ ሆ አረጋግጠዋል።

ያሁኑ የስኬት ዜና የተሰማው የ”ኑሪ” የመጀመሪያ ሙከራ ካሁን ቀደም ከተሰናከለበት ድንገት ስምንት ወራት በኋላ ነው። ከዛሬው የተሳካ ሙከራዋ በኋላ ደቡብ ኮሪያ መንኩራኩር ወደ ህዋ በማምጠቅ አስረኛዋ ሃገር ሆናለች።

ይህ ችሎታ እና ልምድ የመንኩራኩር ማምጠቂያ መሳሪያዎች እና የቦለስቲክ ሚሳዮሎች በርካታ የሚጋሯቸው ገፅታዎች ስላሏቸው ጦር መሳሪያ ለመስራትም ያግዛል።

XS
SM
MD
LG