በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ከስድስት ወር በላይ ለሆኑ ህጻናት የኮቪድ 19 ክትባት መስጠት ልትጀምር ነው


ይህ በመስከረም 14/2021 የተነሳ ምስል ቤንሳልቬኒያ የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ ክትባት ሲሰጡ ያሳያል።
ይህ በመስከረም 14/2021 የተነሳ ምስል ቤንሳልቬኒያ የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ ክትባት ሲሰጡ ያሳያል።

ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት ቅዳሜ ጀምሮ ለጨቅላዎች እና ለትምህርት ላልደረሱ ህጻናት የሚሰጥ የክትባት መርሀ-ግብር ክፍት አድርጋለች። በሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መሰጠት የሚጀምረው ክትባት፣ የሀገሪቱን የክትባት ዘመቻ ዕድሜያቸው ከስድስት ወር በላይ እስከ ሆኑ ህጻናት ድረስ ያሰፋል።

የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል አማካሪዎች ለጨቅላዎች ክትባቱ እንዲሰጥ ያቀረቡት ምክረ-ሀሳብ ፣ በማዕከሉ ዳይሬክተር ዶ/ር ሮቼል ዋልንስኪ ፊርማ ጸድቋል።

በርካታ ወላጆች እና እንክብካቤ ሰጪዎች ህጻናት ልጆቻቸውን ለማስከተብ ጓጉተዋል ። በዛሬው ውሳኔ መሰረት ይሄን ማድረግ ይቻላቸዋል ” ብለዋል ዋልንስኪ በመግለጫቸው ።

ለክትባቶች ዕውቅና የሚሰጠው የአሜሪካ የምግብ እና የመድሐኒት አስተዳደር ቢሆንም ፣ ለማን መሰጠት እንዳለበት የሚወስነው ግን የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ነው

ክትባቶቹ ህጻናትን ለአልጋ ከመዳረግ፣ ከሞት ብሎ እስካሁን ግልጽ ካልሆኑ ከተራዘመ የጤና እክሎች እንደሚታደጓቸው ፣ የሲዲሲ አማካሪዎች ቡድን ገልጿል።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ክትባትን ለማስፋፋት አቅሙን ያጠናከረ ሲሆን ፣ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ክትባቶች በሀገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ ለሀኪሞች ፣ ለሆስፒታሎች እና ለማህበረሰብ የጤና ክሊኒኮች እንዲደርሱ ታዟል።

በአሁኑ ዘመቻ በግርድፉ 18 ሚሊየን ህጻናት ለክትባት ብቁ ይሆናሉ የተባለ ሲሆን ምን ያህሉ ይከተባሉ የሚለውን ግን ለወደፊቱ የሚታይ እንደሆነ ተጠቁሟል።ዕድሜያቸው ከ5-11 ለሆኑ ህጻናት ክትባት መሰጠት ከተጀመረ ወዲህ ክትባቱን የወሰዱት ቁጥር ከ አንድ ሶስተኛ ያነሰ ነው ።

ዘገባው የአሶሼትድ ፕረስ ነው።

XS
SM
MD
LG