በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ጤና ድርጅት 'የዝንጅሮ ፈንጣጣ' በሽታን ስም በመቀየር ዙሪያ ሊወያይ ነው። 


ፋይል - የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከ እ.አ.አ በ2003 ያወጣው ሞላላ ቅርፅ ያለው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስን የሚያሳይ ምስል
ፋይል - የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከ እ.አ.አ በ2003 ያወጣው ሞላላ ቅርፅ ያለው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስን የሚያሳይ ምስል

በዚህ አመት ብቻ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ መያዛቸው የተረጋገጠ እና አንድ ሺህ አምስት መቶ ደግሞ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተጠረጠሩ ሰዎች ከሰባት ቫይረሱ ለአመታት ከኖረባቸው ሀገራት እና 32 አዲስ ተጠቂ ሀገራት መገኘቱን የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አስታውቅዋል።

በተለይ በሽታው በአውሮፓ መስፋፋቱንና በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች 85 ከመቶ የሚሆኑት የሚገኙት በአውሮፓ መሆኑንም የተቋሙ የአውሮፓ ዳይሬክተር ዶክተር ሃንስ ክሉጋ ገልፀዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት በበሽታው በፍጥነት መስፋፋት ዙሪያ በሚቀጥለው ሳምንት አስቸኳይ ስብሰባ የሚያደርግ ሲሆን የቫይረሱን ስም መለወጥ ያስፈልግ እንደሆንም ይወያያሉ።

በቅርቡ አንድ የሳይቲስቶች ቡድን የበሽታውን መስፋፋት ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ቫይረሱ የአፍሪካ እንደሆነ አድርጎ መዘገብ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን አድሎዋዊ እና አግላይ መሆኑን በመግለፅ 'በተለይ ባደጉት ሀገራት በሚዲያ ስለበሽታዊ ሲዘገብ የአፍሪካዊ ህመምተኞችን ምስል ማሳየቱ የዚህ አንድ ማሳያ ነው" ብለው ነበር።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በብዛት ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ቫይረስ ሲሆን፣ ከሰው ወደ ሰውም ከሰውነት በሚወጡ ፈሳሾች፣ ቆዳ ላይ በሚኖር ቁስል፣ ከአፍ፣ ጉሮሮ እና መተንፈሻ አካላት በሚወጡ ነጠብጣቦች እና ሌሎች በተነካኩ እቃዎች አማካኝነትም ሊተላለፍ ይችላል።

XS
SM
MD
LG