በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል የሚገኝ የሲክ ማህበረሰብ የፀሎት ቤት ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሰባት መቁሰላቸውን የታሊባን ባለስልጣናት ዛሬ አስታወቁ።
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አብዱል ናፊ ታኮር ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ጠመንጃ የያዙ ቡድኖች የአምልኮት ስፍራውን ይጠብቁ የነበሩ የፀጥታ ሀይሎች ላይ ጥቃት ከከፈቱ በኃላ ወደ ውስጥ መግባታቸውን እና የሲክ ማህበረሰብ አባት እና የፀጥታ ሀይሎች መገደላቸውን ገልፀዋል።
ታጣቂዎቹ ፈንጂ የጫነ መኪና ህዝብ ወደተሰበሰበበት ስፍራ ለመንዳት ሙከራ ቢያደርጉም፣ ያሰቡት ቦታ ሳይደርሱ ፈንጂው አስቀድሞ በመፈንዳቱ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ መቅረቱን ታኮር አስረድተዋል።
ለጥቃቱ እስካሁን ሀላፊነት የወሰደ ወገን የለም።