በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ የፀጥታ ኃይሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈፀማቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ


የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

በጋምቤላ ክልል፣ ጋምቤላ ከተማ የተከሰተውን የፀጥታ እና ይደህንነት ችግር ተከትሎ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት የኃይል ርምጃ ነዋሪዎች ለተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መጋለጣቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀውና ሸኔ ብሎ የሚጠራው፣ እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን ከጋምቤላ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎች ጋር በመሆን በጋምቤላ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ የመንግስት የፀጥታ አካላት ርምጃ መውሰዳቸውን የክልሉ መንግስት ቢያስታውቅም ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ እስካሁን ድረስ በከተማው የተሟላ መረጋጋት አለመስፈኑን፣ የነዋሪዎች የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ አለመጀመሩን፣ እንዲሁም የንግድ አካባቢዎችን ጨምሮ በአንዳንድ ስፍራዎች ዘፈፋ እንደተፈሰመ ነዋሪዎች መግለፃቸውን አመልክቷል።

በተጨማሪም ከሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በጥቃቱ ተሳትፈዋል ወይም ተባብረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ቤት በመሄድ ግድያዎች እንደፈፀሙ ኢሰመኮ ከምስክሮች እና የተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃዎች ማግኘቱን ገልጿል።

የፀጥታ ሀይሎች የሰዎችን ደህንነት እና የከተዋን ሰላም ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን እንደሚገባ የገለፀው የኢሰመኮ መግለጫ ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል ርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠቡ እና ህገወጥ ተግባራት ያካሄዱ አባላት ተጣርተው ተጠያቂ እንዲሆኑም አሳስቧል።

XS
SM
MD
LG