በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦኤንኤን ጋዜጠኞች እና የኦነግ አመራሮች እንደገና ለብይን ተቀጠሩ


የኦኤንኤን ጋዜጠኞች እና የኦነግ አመራሮች እንደገና ለብይን ተቀጠሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:53 0:00

የኦኤንኤን ጋዜጠኞች እና የኦነግ አመራሮች እንደገና ለብይን ተቀጠሩ

ላለፉት ሰባት ወራት በእስር ላይ የሚገኙት እና “ከሕግ አግባብ ውጪ መንግሥትን ከሥልጣን ለማስወገድ ተንቀሳቅሳችኋል” በሚል ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኘው ሁለት የኦሮሚያ ኒውስ ኔትዎርክ (ኦኤንኤን) ጋዜጠኞች እና 15 የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አመራሮች በድጋሚ ለብይን ተቀጠሩ።

የኦሮምያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዝገቡን ለዛሬ ቀጥሮት የነበረው፤ የኦሮምያ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎት እንደሆነ ለመስማት ነበር።

የጋዜጠኞቹ ጠበቃ አቶ ጉደኔ ፍቃዱ፤ ሁለቱ የኦሮሚያ ኒውስ ኔትዎርክ (ኦ ኤን ኤን) ጋዜጠኞች ደሱ ዱላ እና ቢቅላ አመኑ እንዲሁም ከእነርሱ ጋር የተከሰሱት 15 ተጠርጣሪዎች አዲስ አበባ ሳር ቤት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው በኦሮሚያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ መቅረባቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

“የመጀመርያው ክስ ተሰርዟል፣ ከዚያ በኋላ አሻሽለው ያቀረቡት ክስም ሕጋዊ መሰረት የለውም። ፍርድ ቤቱ በዛሬዉ ችሎት ተጠርጣሪዎቹ ላይ አሁንም የቀረበ ክስ አለመኖሩን አረጋግጧል።" ካሉ በኋላ "እኛም ተጠርጣሪዎቹ ላይ ወንጀል ከሌለ በነፃ እንዲለቀቁልን ብንጠይቅም አሁንም ችሎቱ በራሱ ፍቃድ አቃቤ ሕግ ክሱን እንዲያሻሽል ሲል ብይን ሰጥቶ ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።ችሎቱ ይህንን ክስ ውድቅ አርጎ ተጠርጣሪዎቹን መልቀቅ ሲገባው እንደገና ወደዚህ ውሳኔ መጥቷል።” ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በመጀመርያው ክስ፣ በሕዝብ የተመረጠን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ለመናድ አሲረዋል፣የሽግግር መንግሥት ሰነድን አዘጋጅተዋል እና በአጠቃላይ መንግስትን በኃይል ለመናድ ሞክረዋል የሚል የሚሉ ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ጠበቃው አስታውሰዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ከኅዳር 8/2014 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG