በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካሕዴኅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልን የዋና ከተሞች አወቃቀር ዕቅድ ተቃወመ


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ህዝበ ውሳኔ ማስተባበሪያ ቢሮ ቦንጋ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ህዝበ ውሳኔ ማስተባበሪያ ቢሮ ቦንጋ

“ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፣ የብዝኀ ከተሞች የአወቃቀር ሥርዓትን ለመተግበር እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፤” ያለው የካፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት/ካሕዴኅ/፣ ለዐዲሱ ክልል ከአንድ በላይ ዋና ከተሞችን ለማደራጀት የታቀደው ሥርዓት፣

“ከሕዝቡ ፍላጎት ውጭ እና ሕዝቡ በውል ያልተስማማበት ነው፤” ሲል ተቃወመ።

የክልሉ ባለሥልጣናት ስለ ኅብረቱ ተቃውሞ አስተያየት ለመስጠት ባይሹም፣ ሰሞኑን ለደቡብ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የግብርና ቢሮ ሓላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣

“የብዝኀ ከተሞች አደረጃጀት፣ በአንድ የጋራ ክልል ለመኖር የተሰባሰቡ ሕዝቦችን አሳታፊ እና ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፤” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተሉት የተናገሩ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ አቶ ዳያሞ ዳሌ፣ አንድ ክልል ከአንድ በላይ ዋና ከተሞች ቢኖሩት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አስረድተዋል።

ለአንድ ክልል ከአንድ በላይ ዋና ከተሞችን ማዋቀር፣ ለፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እና እድገት ሊረዳ እንደሚችል የሚናገሩት፣ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ረዳት ፕሮፌሰር ሽመልስ አሻግሬ በበኩላቸው፣ ለብዝኀ ከተሞች አወቃቀር ሥርዓት አዎንታዊ እይታ እንዳላቸውና ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ጎልቶ እንደሚታያቸው ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

ካሕዴኅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልን የዋና ከተሞች አወቃቀር ዕቅድ ተቃወመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:09 0:00

XS
SM
MD
LG