ማላዊ ውስጥ ህፃናትን አስከፊ በሆነ ምስል እየቀረጸ ሲሸጥ የተገኘውን ቻይናዊ የአገሪቱ መንግሥት በአስቸኳይ አስሮ ከሀገር እንዲያስወጣው የመብት ቡድኖች አሳሰቡ።
ማላዊ ውስጥ ህፃናትን አስከፊ በሆነ ምስል እየቀረጸ ሲሸጥ የተገኘውን ቻይናዊ የአገሪቱ መንግሥት በአስቸኳይ አስሮ ከሀገር እንዲያስወጣው የመብት ቡድኖች አሳሰቡ።
ቢቢሲ ባካሄደው ክትትል “ሉኬ” የተባለው ቻይናዊ እንዲዘምሩ እና በማንዳሪን ቋንቋ ተናገሩ እያለ በቪዲዮ በመቅዳት በኢንተርኔት ላይ እንደሚሸጥ ደርሶበታል።
ሰውየው በቀን በቀን በመቶዎች የተቆጠሩ ቪዲዮዎች እየቀረጸ እያንዳንዱን ሰባ ሰባ ዶላር እንደሚሸጥ እና ለልጆቹ ግን ሃምሳ ሳንቲም እንደሚሰጣቸው ቢቢሲ ያደረገው ክትትል አመልክቷል።
ህፃናቱን በማንዳሪን ቋንቋ የቻይና ህዝብን እንዲያሞግሱ፣ በድህነት ላይ እንዲያፌዙ እንዲሁም "እኔ ደደብ ጥቁር አውሬ ነኝ" እያሉ እንዲዘምሩ ያስተማራቸው መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።
በማላዊ የቻይና ኤምባሲ ድርጊቱን ማውገዙ ተገልጿል።