በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ለሶማሊያ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ቪክቶሪያ ኑላንድ ትናንት ሰኞ በሞቃዲሾ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ የፀጥታ፣ የመልሶ ዕርቅ እና የለውጥ አጀንዳዎቻቸውን እንደምትደግፍ የገለጹላቸው መሆኑን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ቢሮ የወጣው መግለጫ አስታውቋል። በተጨማሪም ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ እና በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄዱ ፀረ ሽብርተኛ ጥረቶች መደገፏን እንደምትቀጥልም የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ሚኒስትር ኑላንድ ገልጸውላቸዋል።

ሶማሊያ የተደቀነባትን ከባድ ድርቅ እና የምግብ እጥረት በተመለከተም የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የድርቅ ምላሽ ልዩ ተወካይ አብዲራህማን አብዲሻኩር ዋርሳሜ እንዲሁም የምግብ እና የግብርና ድርጅት ዩኒሴፍ እና የዓለም የጤና ድርጅትን ጨምሮ ከተመድ ተቋማት ተጠሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

መግለጫው በማስከተል የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለአፍሪካ ቀንድ በመደበው ወደ 105 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ አዲስ ሰብዓዊ ድጋፍ በሶማሊያ የከበደ ረሃብ ለመከላከል የሚያስፈልግ አጣዳፊ የምግብ እርዳታ እና ሊሎችም ሰብዓዊ ድጋፎችን ለመስጠት ያለውን ዕቅድ ያለው መሆኑን ምክትል ሚኒስትር ኑላንድ መግለጻቸውን አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG