በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ እና ሱዳን ጋር ውይይት ለመቀጠል ፍቃደኛ ነኝ አለች


Ethiopian Dam Starts Generating Power - GERD
Ethiopian Dam Starts Generating Power - GERD

በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለውን በአፍሪካ ግዙፍ የሆነ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃየል ማመንጫ በተመለከተ ኢትዮጵያ ከግብጽ እና ሱዳን ጋር ውይይት ለመቀጥል ፍቃደኛ መሆኗን ከፍተኛ የኢትዮጵያ ባለስልጣን አስታወቁ።

በግድቡ ጉዳይ ቀድሞ ተደራዳሪ የነበሩት እና በአሁን ሰዓት በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ስለሺ በቀለ በዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከሆኑት ማይክ ሃመር ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ነው ይሄን አስተያየት የሰጡት።

ትላንት አርብ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አምባሳደሩን ጠቅሶ “ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ሕብረት የሚመራ የሶስትዮሽ ድርድር ለማስቀጠል ፍቃደኛ ናት” ብሏል።

ከዚህ ቀደም ሶስቱ ሃገራት የተለያዩ ድርድሮችን ቢያካሂዱም ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ግብጽ የግድቡ መሙላት ናይል በግብጽ ያለውን የውሃ መጠን ይቀንሰዋል ብላ ትሰጋለች። ባለፈው የካቲት ወር ላይም ኢትዮጵያ ከአንደኛው የግድቡ ክፍል ሃይል ማመንጨቷን አስታውቃለች።

በተመሳሳይ ትላንት አርብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዘንድሮም ሶስተኛው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌት እንደሚካሄድ ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል። አምባሳደሩ አያይዘውም “ከግድቡ ግምባታ ጀምሮ እንዳስታወቅነው የሶስትዮሽ ውይይት ይቀጥላል” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG