በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደራሼና አማሮ አዋሳኝ ላይ ስላለው ሁኔታ ነዋሪዎች ይናገራሉ


ደራሼና አማሮ አዋሳኝ ላይ ስላለው ሁኔታ ነዋሪዎች ይናገራሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:32 0:00

ደራሼና አማሮ አዋሳኝ ላይ ስላለው ሁኔታ ነዋሪዎች ይናገራሉ

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ደራሼና አማሮ ልዩ ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ከአማሮ አቅጣጫ ይተኮሳል ባሉት ጥይት አራት ሲቪሎች መገደላቸውንና ከ15 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን የደራሼ ነዎሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ተናግረዋል።

በአማሮ በኩል የፀጥታ ችግር ካለባቸው አቡሎ አልፋጮና ቡኒቲ ቀበሌዎች ባለፉት ሦስት ዓመታት ከሰላሣ ሺህ በላይ ሰው መፈናቀሉን ነዋሪዎቹ ገልፀው የተባለው ግድያ ስለመፈፀሙ እንደማያውቁ የቀበሌዎቹ ነዋሪዎች አመልክተዋል።

ግድያ፣ ዘረፋና ንብረት ማወደም ላይ የተሰማሩ ሲሉ ነዋሪዎቹ የከሰሷቸው “ጎማይዴ”የሚባል አዲስ ልዩ ወረዳ እንዲመሠረት በኃይል እንደሚንቀሳቀሱ አመልክተው ከአማሮ ልዩ ወረዳ አቅጣጫ ይተኮሳል የተባለውን አጣጥለዋል።

በአካባቢው ግጭት ቢኖርም ከክልሉ የመንግሥት አካላት ይህንን የሚያረጋግጥ መረጃ ማግኘት እንዳልቻለ ዮናታን ዘብዴዎስ ከሃዋሳ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG