በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሦስት የሚዲያ ባለሞያዎች የዋስትና ይግባኝ ክርክር ለውሳኔ ተቀጠረ


የሦስት የሚዲያ ባለሞያዎች የዋስትና ይግባኝ ክርክር ለውሳኔ ተቀጠረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:28 0:00

የሦስት የሚዲያ ባለሞያዎች የዋስትና ይግባኝ ክርክር ለውሳኔ ተቀጠረ

የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ ፣ የ“ገበያኑ” ዩቲዩብ ሚዲያ መስራች እና አዘጋጅ ሰለሞን ሹምዬ እና የ”ሮሃ”ዋ መዓዛ መሐመድ 10 ሺሕ ዋስ አስይዘው እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ትናንት ትዕዛዝ ቢሰጥም፣ ፖሊስ ዋስትናውን በመቃወም ይግባኝ በመጠየቁ ምክንያት አልተፈቱም፡፡

በዛሬው ዕለት የፖሊስን ይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ፣ ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በሦስቱ የሚዲያ ባለሞያዎች ላይ የቀረበውን የዋስትና ይግባኝ ለመመልከት ዛሬ ጠዋት የተሰየመው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ፖሊስ ያቀረበውን አቤቱታ አዳምጧል።

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ትናንት ግንቦት 30/2014 ዓ.ም ለሦስቱ የሚዲያ ባለሞያዎች የተፈቀደው የ10 ሺሕ ብር ዋስትና ውድቅ ተደርጎ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲሰጡት ጠይቋል።

ዛሬ ችሎት የተገኙት “ገበያኑ” የተሰኘው ዩቲዩብ ቻናል አዘጋጅ ሰለሞን ሹምዬ ጠበቃ አቶ በፍቃዱ ስዩም የነበረውን የዋስትና ይግባኝ ክርክር ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል።

መርማሪ ፖሊሶች ዋስትናው ተሽሮ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጣቸው በምክንያትነት ያቀረቡት፣ የሚዲያ ባለሞያዎቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል “ውስብስብ በመሆኑ ነው” የሚል ነው።

ፖሊስ የጠየቀውን ይግባኝ የተቃወሙት የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች በበኩላቸው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤት የፈቀደውን ዋስትና እንዲያጸና በመጠየቅ የተከራከሩ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ነገ ሰኔ 2/2014 ዓ.ም ውሳኔውን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ትናንት ግንቦት 30/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ የፍትሕ መጽሔት ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ እንዲሁም የተለያዩ የዩቲዩብ ሚዲያዎች መስራች እና አዘጋጅ የሆኑት ሰለሞን ሹምዬ እና መዓዛ መሐመድ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር እና የተጠቀሰውን የዋስትና ገንዘብ አስይዘው ከእስር ለመውጣት በሂደት ላይ በነበሩበት ወቅት ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቁ ምክንያት ሳይፈቱ መቅረታቸውን ትላንት መዘገባችን ይታወሳል።

/ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ/

XS
SM
MD
LG