በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ተገለፀ


በአማራ ክልል በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:51 0:00

በአማራ ክልል በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ተገለፀ

መንግስት የሕግ ማስከበር ዘመቻ ብሎ በጠራው እና ከአራት ሳምንታት በፊት በጀመረው እንቅስቃሴ በአማራ ክልል በቁጥጥር ሰር ከዋሉት ውስጥ አብዛኛዎቹ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ቤተሰቦቻቸው እና አንድ የሕግ ጠበቃ አስታውቀዋል ።

በክልሉ ለፍርድ ሳይቀርቡ እስከ 22 ቀን የሞላቸው ታሳሪዎች እንደሚገኙ የተጠርጣሪ ቤተሰቦች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ጠበቆች ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣቸው መግለጫዎችም ሕጋዊ ያልሆኑ ያላቸውን አካሄዶች ተችቷል።

ሰሞኑን መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በበኩላቸው የህግ ማስከበሩ እንቅስቃሴ ልዩ ዘመቻ በመሆኑ የፍትህ ሂደቱ ሊጓተት ይችላል ብለዋል

የአማራ ክልል መንግሥት በክልሉ በፋኖ ስም ግድያ ፣ ዝርፊያ የሰዎች ዕገታ እና መስለ ሕገ ወጥ ወንጀሎችን በመፈፀም ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን ከ4ሺ 500 በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ማስታወቁ ይታወሳል።

/ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ/

XS
SM
MD
LG