በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በማኅረሰቡ ላይ የሚያሳድሩት ጫና ምንድነው?


በኢትዮጵያ ግጭቶች እና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በማኅረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ መሆኑን እና ወደፊትም መጥፎ ጠባሳ ጥለው እንደሚያልፉ የሰብዓዊ መብቶች ባለሞያዎች ተናገሩ።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው ጦርነት እንዲሁም በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ከብሔር ማንነት፣ ራስን በራስ የማስተዳደርና የአስተዳደር አካባቢዎች ወሰን በሚመለከት አልፎ አልፎም ከኃይማኖት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ወቅቶች የሚያገረሹ ግጭቶች ኢትዮጵያውያንን ለከፋ ጉዳት እንደዳረጋቸው በየጊዜ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ።


ፆታዊ እና ወሲባዊ ጥቃቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ሰዎች ለሞት፣ ለአካልና ለሥነ ልቦና ጉዳት፣ እንዲሁም ለመፈናቀልና፣ ለንብረት ውድመት መዳረጋቸውን በመንግሥት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ገልጿል።


እነዚህ በኅብረተሰቡ አስተሳሰብም ሆነ አእምሯዊ የጤና ሁኔታ ላይ የሚያስከትሏቸው ችግሮች ይኖሩ ይሆን? የሚል ጥያቄን ይዘን ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ አጥኚ አቶፍሰሃ ተክሌ እና በኢትዮጵያየሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ያሬድኃ/ማርያምን ጋራ ቆይታ አድርገናል።

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በማኅረሰቡ ላይ የሚያሳድሩት ጫና ምንድነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:52 0:00

XS
SM
MD
LG