ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ውስጥ በነበረው ግጭት ምክንያት ተፈናቅለው በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተጠልለው ከነበሩ ተፈናቃዮች መካከል አብዛኞቹ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናገሩ።
በአማራ ክልል ጓንጓ ወረዳ በግለሰብ ቤቶች እና ቻግኒ ከተማ አስተዳደር በተዘጋጀ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው ከነበሩ ከ75ሺ በላይ ተፈናቃዮች ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት ባለፍት ሁለት ወራት ውስጥ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ባለሥልጣናቱ ገልፀዋል።
የጉምዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር አቶ ግራኝ ጉደታ መንግሥት በአካባቢው ሰላም ለማምጣት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ ገልፀዋል።
ዘገባው የአስቴር ምስጋናው ነው።