በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር የትምምን ነፈጋ ድምፅ ሊሰጥባቸው ነው


የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን

የብሪታኒያ ገዢው ወግ አጥባቂ ፓርቲ ዛሬ ሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ከሥልጣናቸው ሊያስነሳቸው የሚችል የትምምን ነፈጋ ድምፅ እንደሚሰጥባቸው ተገልጿል፡፡

የፓርቲው ባለሥልጣን ግራም ብራዲ በጆንሰን አመራር ላይ የትምምን ነፈጋ ድምፅ እንዲሰጥ በመጠየቅ ከምክር ቤት አባላት በቂ ደብዳቤዎች የደረሱዋቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የትምምን ነፈጋ ድምጽ አሰጣጥ መጥራት የሚቻለው በህግ አውጪው ምክር ቤት ካሉት የወግ አጥባቂው ፓርቲው አባላት የአስራ አምስት ከመቶው ወይም የሃምሳ አራት አባላት ጥያቄ እንደሚያስፈልግ እስካሁን ከዚያ በላይ የደረሳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጆንሰን 359 ከሚደርሱ ወግ አጥባቂ ህግ አውጭዎች መካከል በቂ ድምጽ ካላገኙ ከፓርቲው በሚመረጥ ሌላ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚተኩ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ጆንሰን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት እንግሊዝ ውስጥ ዝግ የነበረውን ፕሮቶኮል በመጣስ በመንግሥት ህንጻ ውስጥ በተደረገው ድግስ ላይ በመገኘታቸው የተሰነዘረባቸውን የስነ ምግባር ክስ ለማስተባበል ለወራት ሲታገሉ መቆየታቸው ተመልክቷል፡፡

ጉዳዩን ያጣሩ መርማሪዎች እኤአ በ2020 እና 2021 በነበረው የኮቪድ ወረርሽ ወቅት የተላለፈውን መመሪያና ገደብ በመጣስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ህንጻ ውስጥ በሠራተኞች የተዘጋጁ የአልኮል መጠጥ የተቀላቀሉባቸው ድግሶች መካሄዳቸውን አረጋግጧል፡፡

XS
SM
MD
LG