በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ጎግል በዩቲዩብ ቪዲዮ ስማቸው ጠፍቷል ለተባሉት አውስትራሊያው ፖለቲከኛ 515 ሺ ዶላር እንዲከፍል ተፈረደበት

ጎግል በዩቲዩብ ቪዲዮ ስማቸው ጠፍቷል ለተባሉት አውስትራሊያው ፖለቲከኛ 515 ሺ ዶላር እንዲከፍል ተፈረደበት


የአውስትራሊያ ፍርድ ቤት፣ ዛሬ ሰኞ ባስተላለፈው ውሳኔ፣

"የቀድሞው አንጋፋ የምክር ቤት አባል፣ በአንድ የዩቱብ ዝግጅት የሚቀርብ ተንታኝ ያለማቋረጥ ባካሄደባቸው ዘረኛ፣ ዘላፊ እና ስም አጉዳፊ ዘመቻ ምክንያት ከፖለቲካው ዓለም እንዲወጡ አድርጓቸዋል" በማለት ትልቁ የቴክኖሎጂ ኩባኒያ የሆነው የጎግል 515ሺ ዶላር እንዲከፍላቸው ፈርዷል፡፡

የፌዴራሉ ፍርድ ቤት በጉጉሉ አልፋቤት ኩባኒያ ባለቤትነት ስር የሚገኘው ዩቱዩብ በቀድሞ የምክር ቤቱ አባል ላይ በተሰነዘረው ጥቃት፣ በሺህዎቹ የሚቆጠሩ ዶላሮችን ማግኘቱን አመልክቷል፡፡

ከሁሉም የአውስትራሊያ ክፍላተ ሀገር ብዛት ያለው ህዝብ ያላላት የኒው ሳውዝ ዌልስ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ጆን ባሪላሮ እኤአ ከ2020 መጨረሻ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የተላለፈው ቪዲዮ ወደ 800ሺ ጊዜ መታየቱንም ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

በዩቲዩብ ቪዲዮዎቹ ላይ የቀረበው የፖለቲካ ተቺ ጆርዳን ሻንክስ የምክር ቤት አባሉን ያለምንም ማስረጃ ሙሰኛ ብሏቸዋል። ከጥላቻ ንግግር በማይተናነስ ዘረኛ ቃል ዘልፏቸዋል ብለዋል ዳኛው፡፡

የምክር ቤት አባሉ ባለፈው እእአ 2021 ከፖለቲካው ዓለም የወጡት በጉግል እና በሚስተር ሻንክስ ዘመቻ ምክንያት ነው ሲሉም ዳኛው አክለው አስረድተዋል፡፡ የጎግል ቃል አቀባይን ምላሽ ለማካተት አልተቻለም፡፡

XS
SM
MD
LG