በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን ጠቅላይ መሪ 'ጠላቶች' ተቃውሞዎችን እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ ከሰሱ


የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኔ 
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኔ 

የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኔ 'ጠላቶች' ሲሉ የገለጿቸው፣ በተለይ እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ያሉ ሀገራት ተቃውሞዎችን በመጠቀም እስላማዊውን መንግስት ለማዳከም እየሞከሩ ነው ሲሉ ከሰዋል።

ባለፉት ሳምንታት፣ በኢራን የሚታየውን የዋጋ ንረት እና ሙስናን የተቃወሙ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ሲሆን ካሜኔ ዛሬ በቴሌቭዥን ባደረጉት ንግግር "በአሁኑ ወቅት ጠላቶቻችን እስላማዊ ስርዓትን ለማጥቃት እነዚህን ተቃውሞዎች እንደዚህ አይነት ተቃውሞዎችን ይጠቀማሉ " ብለዋል።

ግንቦት 15፣ 2014 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኘው አብዳን ከተማ አንድ በግንባታ ላይ የነበረ ህንፃ ተደርምሶ 37 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የተሳተፉ ሰዎች 'ብቃት የሌላቸው ባለስልጣናት' በሞት እንዲቀጡ ጠይቀዋል።

ካሜኔ በበኩላቸው ጠላቶች የሚሏቸው "ኢንተርኔት፣ ገንዘብና ቅጥረኛ ተዋጊዎች በኩል የስነ-ልቦና መንገዶችን በመጠቀም ህዝቡን በእስልማዊ መንግስት ላይ ለማስነሳት ይፈልጋሉ" ሲሉ ተናግረዋል።

ካሜኔ እ.አ.አ በ1979 በዩናይትድ ስቴትስ ይደገፍ የነበረው የሻ መንግስት ከወደቀ በኃላ የተቋቋመውን እስላማዊ መንግስት የመሰረቱ ናቸው።

XS
SM
MD
LG