በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካሜሩን እና መካከለኛው አፍሪካ በድንበር የሚገኙ ታጣቂዎችን በጋራ ለመዋጋት ተስማሙ 


የካሜሩን ወታደሮች ባሜንዳ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችንና ማህበረሰቡን ለመጠበቅ ተሰማርተዋል (ፎቶ: M. Kindzeka / VOA)
የካሜሩን ወታደሮች ባሜንዳ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችንና ማህበረሰቡን ለመጠበቅ ተሰማርተዋል (ፎቶ: M. Kindzeka / VOA)

የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እና የካሜሩን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የሚካሄደውን ውጊያ ሸሽተው ወደ ካሜሩን የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎችን ሰርገው እየገቡ የሚገኙትን ታጣቂዎች በጋራ ለመዋጋት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። የጦር መሳሪያ ዝውውርንም ለመግታት ወታደሮቻቸውን በጋራ እንደሚያሰማሩም ገልፀዋል።

ባለስልጣናቱ እዚህ ስምምነት ላይ ይደረሱት የመካከለኛው አፍሪካ አማፂያን እና ታጣቂ ቡድኖች በድንበር የሚገኙ ከተሞችንን እና መንደሮችን በመውረራቸው እና ለተለያዩ አቅርቦቶች ሲሉ ጥቃት እያደረሱ ስለሚገኙ መሆኑን አስታውቀዋል።

ካሜሩን የሚገኘው አዳማዋ ክልል አስተዳዳሪ የሆኑት ኪልዳዲ ታጉኤኪ ቡዋካር እንደተናገሩት የሁለቱ ሀገር ፕሬዝዳንቶች አማፂያኑ በሚያደርሱት የከብት ዘረፋ፣ ጠለፋ፣ የመሳሪያ ዝውውር እና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ የደህንነት ስጋቶች ምክንያት በድንበር ከተሞች የሚታየውን የኢኮኖሚ እድገት ማሽቆልቆል ማስቆም ይፈልጋሉ።

XS
SM
MD
LG