በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና፣ ሩሲያ፣ ማይናማር፣ አፍጋኒስታን፣ ህንድ፣ ፓኪስታን የሃይማኖት ነጻነትን ይጥሳሉ ስትል አሜሪካ ከሰሰች


ቻይና፣ ሩሲያ፣ ማይናማር፣ አፍጋኒስታን፣ ህንድ፣ ፓኪስታን የሃይማኖት ነጻነትን ይጥሳሉ ስትል አሜሪካ ከሰሰች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:59 0:00

ቻይና፣ ሩሲያ፣ ማይናማር፣ አፍጋኒስታን፣ ህንድ፣ ፓኪስታን የሃይማኖት ነጻነትን ይጥሳሉ ስትል አሜሪካ ከሰሰች

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዓመታዊ የሃይማኖት ነጻነት ሪፖርቱን ሲያወጣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ማያንማር፣ አፍጋኒስታን፣ ህንድ፣ ፓኪስታንን እና ሌሎች ሃገሮችን ሃይማኖታዊ መብትን በመጣስ ከሷል።

መስሪያ ቤቱ ዓመታዊ የሃይማኖት ነጻነት ሪፖርቱን ለአሜሪካ ምክርቤት ሲያቀርብ አጋር ሀገር የሆነችው ህንድንም በእምነት ቦታዎች ላይ ጥቃት ሲፈጸም በመደገፍ ወይም እንዳላየ በማለፍ ከሷታል። የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዓመታዊ የሃይማኖት ነጻነት ሪፖርቱን ሲያወጣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ማያንማር፣ አፍጋኒስታን፣ ህንድ፣ ፓኪስታንን እና ሌሎች ሃገሮችን ሃይማኖታዊ መብትን በመጣስ ከሷል።

መስሪያ ቤቱ ዓመታዊ የሃይማኖት ነጻነት ሪፖርቱን ለአሜሪካ ምክርቤት ሲያቀርብ አጋር ሀገር የሆነችው ህንድንም በእምነት ቦታዎች ላይ ጥቃት ሲፈጸም በመደገፍ ወይም እንዳላየ በማለፍ ከሷታል። የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አንተኒ ብሊንከንና በመሥሪያ ቤቱ የሃይማኖት ነፃነት ጉዳዮች ዓለምአቀፍ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አምባሳደር ራሻድ ሁሴን ዓመታዊውን ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ሪፖርት ትናንት አቅርበዋል።

በሪፖርቱም በ2021 ዓ.ም. ቻይና መሠረታዊ መብቶችን ከሌሎች ሃገሮች በከፋ ሁኔታ የምትጥስ ሀገር መሆኗ ተጠቅሷል። የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ በተለይ በቻይና በዊገር ጎሳ አባላትና በሌሎችም ላይ ስለሚፈጸመው የመብት ጥሰት ተናግረዋል። “ቻይና በአብዛኛው የእስልምና ተከታይ በሆኑት የዊገር ጎሳ አባላትና በሌሎች አናሳ ጎሳዎች ላይ ዘር የማጥፋትና የጭቆና አካሄዷን ገፍታበታለች። ከአፕሪል ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከ 1 ሚሊዮን በላይ የዊገር፣ ካዝክ፣ ተርኪዝ እና ሌሎችም ጎሳዎች አባላት ሺንጃንግ በሚገኝ የማጎሪያ ሠፈር ውስጥ ይገኛሉ”

ቤጂንግ የሚደርስባትን ዓለም አቀፍ ውግዘት አትቀበልም። ካምፖቹ ‘የሙያ ማሠልጠኛ ማዕከላት ናቸው’ ስትል ትከላከላለች። ብሊንከን በመቀጠል የቻይና ኮሚኒስት መንግስት በቲቤት ቡዲስቶች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ቀጥሎበታል ብለዋል። ኢራንን፣ ማያንማርን፣ የአፍጋኒስታኑን ታሊባን መንግሥትና

ሌሎችንም የአሜርካ ተቀናቃኞችን በመብት ጥሰት ከስሰዋል የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ። አምባሳደር ራሻድ ሁሴን ደግሞ ሩሲያ በዚህ ዓመት በድጋሚ በመብት ጣሾች ዝርዝር ውስጥ ተግኝታለች ብለዋል።

“ባለፈው ዓመት በሪፖርቱ እንደ አሳሳቢ ሀገር የተመደበችው ሩሲያ ሁኔታዎችን ከማሻሻል ይልቅ በሃይማኖት ላይ የምታደርገውን የመብት ጥሰት አባብሳ ቀጥላለች። የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች የሃይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር በሞከሩ ሰዎች ላይ የከፋ የእስር ቅጣት መጣላቸውን ገፍተውበት የቅጣቱ ጊዜ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል። የሩሲያ ባለስልጣኖች በአክራሪነት በሚጠረጠሩ ሰዎች ቤቶች ላይ ከበባዎችን እያደረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍተሻዎች አካሂደዋል። እነዚህ ፍተሻዎች በአብዛኛው ኃይል የተቀላቀለባቸው ናቸው።”

በዓለም ትልቋ ዲሞክራሲ ህንድ ውስጥ በእምነት ተቋማት ውስጥ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እየጨመረ መሆኑን ብሊንከን ሲናገሩ አምባሳደር ራሻድ ደግሞ ሁኔታውን እንዲህ ይገልጹታል። “በህንድ አንዳንድ ባለሥልጣናት እየጨመሩ ያሉ ጥቃቶችን እንዳላየ ማለፍ ብቻ ሳይሆን የሚደግፉበት ሁኔታም አለ”

የህንድ ባለሥልጣናት በሕዳጣን ሃይማኖቶች ተከታዮች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ ከአሜሪካ የሚሰሙ ወቀሳና ነቀፌታዎችን አይቀበሉም።

ብሊንከን በተጨማሪ የህንድ ታሪካዊ ባላንጣ የሆነችውን ፓኪስታንንም አንስተዋል። ባለፈው ዓመት 16 ሰዎች ሃይማኖትን አንቋሽሻችኋል በሚል በተከፈተባቸው ክስ የሞት ፍርድ ተላልፎባቸዋል። ይሁን እንጂ ፍርዱ እስካሁን ተፈፃሚ አልተደረገም።

/ዘገባው የሲንዲ ሴይን ነው፣ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።/

XS
SM
MD
LG