በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቢት ኮይን ምንድነው?


ቢት ኮይን ምንድነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00

ቢት ኮይን ምንድነው?

በርካታ ሰዎች ስለ ክሪፕቶ ከረንሲ ለመረዳት ሲቸገሩ ይስተዋላል። ቢት ኮይን በሚለው ስያሜ ውስጥ 'ኮይን' የሚለው የሚለው ቃል ሰዎች ለዘመናት እቃዎችን ለመግዣ ሲጠቀሙበት የኖሩት ሳንቲም አይነት ትርጉም ያለው ይመስላል።

ሆኖም ቢትኮይኖችም ሆኑ ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎች የኢትንተርኔት ወይም የበይነ መረብ ላይ መገበያያ ናቸው። በቢትኮይን ግብይት ውስጥ ምንም አየነት በእጅ የሚጨበጥ ገንዘብ የለም። ያሉት የተወሰኑ ኮዶችና የሚስጥር ቁጥሮች ብቻ ናቸው።

ሰዎች 'ቢትኮይን ማይኒንግ' ሲሉ ታዲያ ምን ማለታቸው ነው?

በበይነ መረብ ላይ ክሪፕቶከረንሲዎችን በመጠቀም የሚደረግ የክፍያ ልውውጥን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እና መዝግቦ ለማስቀመጥ ብሎክቼይን የተባለ ስርዓት ይጠቀማሉ።

ብሎክቼይን ማለት ለሂሳብ አያይዝ የምንጠቀምበት አይነት ዲጂታል መዝገብ ማለት ነው። ነገር ግን መረጃዎቹ ልክ እንደባንክ ባለ አንድ ቦታ ከመቀመጥ ይልቅ - የሂሳብ መዝገቡ የመገበያያ ገንዘቡን ለሚጠቀሙ ሁሉ እንዲሰራጭ ይደረጋል።

በትክክል ለማስረዳት፣ ብሎክቼይን የሚሰራበት መንገድ ይህን ይመስላል:

አዲስ ክፍያ ሲፈፀም፣ ብሎክቼይኑ ላይ ይመዘገባል። የስርዓቱን ደህንነት ለማረጋገጥ ማንኛውም በገበያ ትስስሩ ውስጥ ያለ ሰው ተመሳሳይ መረጃ ይደርሰዋል።

አዲስ የሚፈፀም ክፍያ ከሌሎች የቅርብ ግዜ ክፍያዎች ጋር አንድ ላይ ተደምሮ አንድ 'ብሎክ' ወይም እስር ይፈጥርና ወደ ብሎክ ቼይኑ ለመመዝገብ ይጠብቃል።

'ማይኒንግ' ተብሎ የሚጠራው የማጣራት ሂደት የሚጀምረው ታዲያ እዚህ ጋር ነው።

'ማይነርስ' የሚባሉት - ማናቸውም በግብይት ትስስሩ ውስጥ የሚገኙ እና በቂ ከኮምፒውተር ጋር ግንኙነት ያለው እውቀት ያላቸው ሰዎች ሆነው አዲስ የገባው ክፍያ ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ እና ለአንድ ብሎክ ወይም እስር በልዩነት የሚሰጠውን ሚስጥራዊ ኮድ ለማግኘት የሚሽቀዳደሙ ናቸው።

ይህ ሂደት ደግሞ ለአንድ ብሎክ ወይም እስር የሚሰጠውን ተበታትኖ የተቀመጠና በጣም ረጅም ቁጥሮችንና ፊደሎችን የያዘ ሚስጥራዊ ኮድን መገመት ይጠይቃል።

ይህ የቤት ስራ 'ፕሩፍ ኦፍ ወርክ' ወይም የስራ ማረጋገጫ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በጣም ውስብስብ እና ደጋግሞ በመሞከር ብቻ የሚገኝ ፣ እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው የኮምፒውተር ማቀነባበሪያ ጊዜ የሚፈጅ ነው። የስራ ማረጋገጫው ብሎክቼይኑን ከማጭበርበር የመጠበቂያ መንገድ ነው።

አዲሱ እስር ወደ ብሎክ ቼይኑ ወይም የሂሳብ መዝገቡ የሚገባው ተበታትኖ የተቀመጠው ሚስጥራዊ ኮድ ሲገኝና የክፍያው ትክክለኛነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

ይህን በማድረግ እድል የቀናው 'ማይነር ' ታዲያ ለስራው በቢትኮይን ይከፈለዋል።

ይህንን ክፍያን የማጣራት እና ስርዓቱን የመጠበቅ ሀላፊነት አዳዲስ ቢትኮይኖች ወደ ገበያ እንዲመጡ ማድረጊያ መንገድ ሲሆን እና በርካታ ተጠቃሚዎቹም ትስስሩን እንዲቀላቀሉ የማበረታቻ ክፍያም ሆኖ ያገለግላል።

በርካቶች ወደ ትስስሩ መምጣታቸውን ተከትሎ ግን የስራ ማረጋገጫ ስራው በየጊዜው የበለጠ አስቸጋሪ እንዲሆን ይደረጋል። ቢትኮይን ማይኒንግ ገና በጀመረበት ጊዜ ተጠቃሚዎች የግል ኮምፒውተራቸውን በመጠቀም ቢትኮይኖችን ለመሰብሰብ ይሞክሩ ነበር።

አሁን ግን አብዛኛው የማይኒንግ ወይም የማጣራት ስራ የሚሰራው ለዚህ ተብለው በተዘጋጁ ትላልቅ የመረጃ ማዕከላት ውስጥ ሲሆን - የእርሻ ቦታ ተብለው ይጠራሉ።

የማጣሪያ እርጃዎቹ እጅግ በጣም ግዙፍ ሀይል ይጠቀማሉ። አንድ የመረጃ ድህረገፅ እንዳመለከተው አንድ ቢትኮይንን ለማጣራት በሰዓት 2ሺህ 156 ኪሎዋት ሀይል ይወስዳል። ይህ አንድ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኝ መካከለኛ መጠን ያለው ቤተሰብ ለ74 ቀን የሚጠቀምበት ሀይል ማለት ነው። የካምብሪጅ ዩንቨርስቲ ጥናት እንደሚያሳየውም አጠቃላይ የቢትኮይን ግብይት ትስስር በዓመት ውስጥ በሰዓት እስከ 131.4 ቴራዋት ሊጠቀም ይችላል።

ቢትኮይን አገር ቢሆን ኖሮ የሚወስደው ሀይል መጠን 106 ሚሊየን ህዝብ ያላት ግብፅ ከምትጠቀመው የሀይል መጠን ጋር ተመጣጣኝ ይሆን ነበር።

በአሁኑ ወቅት ከቢትኮይን ሌላ ከ2ሺህ በላይ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ ስርዓቶች አሉ። አንዳንዶቹ የግብይት ስርዓቱን ከስጋት ነፃ ለማድረግ ከፍተኛ ሀይል የማይፈልጉ ሌሎች አማራጮችን ይጠቀማሉ።

ለምሳሌ አቴሪየም የሚባለው የክሪፕቶከረንሲ አይነት ፕሩፍ ኦፍ ስቴክ ተብሎ ወደሚጠራ ስርዓት የተሸጋገረ ሲሆን ይህም በቂ ገንዘብ ያላቸው ተጠቃሚዎች በዘፈቀደ ተመርጠው እስሮችን ወደ ሂሳብ መዝገቡ እንዲያስገቡ የሚደረግበት መንገድ ነው።

የትኛውም የበይነ መረብ መገበያያ መንገድ የወደፊት ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ግን የሀይል አጠቃቀሙን ችግር መፍታት ወሳኝ ነው።

XS
SM
MD
LG