በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋና አንድ የፓርላማ አባል በምርጫ ወረዳቸው ውስጥ የጾታ ጥቃት ሰለባዎችን የምርመራ ክፍያ ሰረዙ


በጋና አንድ የፓርላማ አባል በምርጫ ወረዳቸው ውስጥ የጾታ ጥቃት ሰለባዎችን የምርመራ ክፍያ ሰረዙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:05 0:00

በጋና አንድ የፓርላማ አባል በምርጫ ወረዳቸው ውስጥ የጾታ ጥቃት ሰለባዎችን የምርመራ ክፍያ ሰረዙ

የአስተም ቤተስብ በጋና ሰሜን ቶንጉ አውራጃ አንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሶስት ሴት ልጆች አሏቸው። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የሁሉም ታናሽ የሆነችው የ15 ዓመቷ ልጅ ተጠልፋ አስገድዶ መድፈር ተፈጽሞባታል።

“የ14 ዓመት ልጅ ፎቶን ከስልኩ ላይ ለእህቴ አሳይቶ ከእርሱ ጋር ወሲብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆኗ እንደገደላት ነገራት። እርሷም እምቢ የምትል ከሆነ እንደሚገላት ዛተ። በሽጉጡ ሰደፍ ደርቷን መታት፤ ሊያንቃትም ሞከረ። ፊቷ እስከሚያብጥ ደበደባት” ስትል አይሪን አትሰም የጥቃት ሰለባዋ እህት ለቪኦኤ ተናግራለች።

የአይሪን እህት ከሰባት ቅናት በፊት ከሆስፒታል ወጥታለች። ከስድስት ወራት በኋላ ደግሞ የክትትል ቀጠሮ አላት። የህክምና ወጪው በብሄራዊ የጤና መድህን ፕሮግራሙ አልተሸፈነም።

“እድሚያቸው ልግብረ ስጋ ግንኙነት ካልደረሰ ልጆች ጋር የሚደረግ ግንኙነት፣ አስገድዶ መድፈርና የጾታ ትንኮሳን በተመለከተ የጤና መድህን ወጪውን አይሸፍንም። ማንኛውም ምርመራ የሚደረግ ከሆነ ወጪውን የምትሸፍነው እራሷ ተጠቂዋ ነች። ወይም ደግሞ ገንዘቡን ከሆነ ቦታ ማምጣት አለባት” ይላሉ የሰሜን ቶንጉ የህክምና ማዕከል ዶ/ር በርናርድ አቱጉባ።

የበብሄራዊ የጤና መድህን ፕሮግራም ባለስልጣን ለቪኦኤ እንደተናገሩት ፕሮግራሙ የጾታ ጥቃትን እንደ ጤና ችግር ሳይሆን እንደ ወንጀል ድርጊት ነው የሚቆጥረው።

የሰሜን ቶንጉ አውራጃ የህዝብ ተወካይ ሳሙኤል አብላክዋ ይህ ኢፍትሃዊ ነው ይላሉ። ተወካዩ በምርጫ ክልላቸው ላሉ ሆስፒታሎች ተጠቂዎችን የምርመራ እናዳያስከፍሉ አዘው ቢሯቸው ወጪውን እየከፈለ ይገኛል።

“እኔ እያሳየሁ ያለሁት በአንድ የምርጫ ክልል ማድረግ እንደሚቻል ነው። አሮጌውን ድንብ አግደናል። ሌሎች አካባቢዎችም ይህን እንዲከተሉና ክፍያውን ለማስቀረት ከጓዶቼ ጋር ህግ ለማርቀቅ እየተነጋገርኩ ነው” ሲሉ ያክላሉ የህዝብ ተወካዩ።

በ 2020 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የተሰራው ጥናት እንዳመለከተው በጋና ከጾታዊ ጥቃት በኋላ ፍትህን የሚፈልጉ ተጠቂዎች ከገቢያቸው ከ 10 እስከ 55 በመቶ እንዲያወጡ ይገደዳሉ። ይህም ተጠቂዎች ፍትህን ፍለጋ ወደፊት እንዳይመጡ ያደርጋል።

የፓርላማ አባሉ ሳሙኤል አብላክዋ ግባቸው ተጠቂዎች ፍትህን ሲሹ ቀላል እንዲሆንላቸውና የጥቃቱ ፈጻሚዎች ድግሞ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ነው።

“ምንም ሁን ማን ወይም ምንም ያህል ገንዘብ ይኑርህ ይህ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው። ከአሁን በኋላ ምንም ትዕግስት የለንም” ብለዋል አብላክዋ።

በዚህ አዲስ ደንብ መሰረት የአትሰም ቤተስብ የጥቃት ፈጻሚው ላይ ክስ ለመመስረትና ፍትህን ለማግኘት ተስፋ ያደርጋል።

XS
SM
MD
LG