በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻድ አጣዳፊ የምግብ ችግር ላይ እንዳለች አውጃ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ተማጸነች


ፎቶ ፋይል - ግለሰቧ ጎዳና ላይ እርዳታ ሲለምኑ፤ በኒጃሜና፣ ቻድ እአአ ሚያዚያ 26/2021
ፎቶ ፋይል - ግለሰቧ ጎዳና ላይ እርዳታ ሲለምኑ፤ በኒጃሜና፣ ቻድ እአአ ሚያዚያ 26/2021

የባህር በር የሌላት ድሃይቱ ሀገር ቻድ አጣዳፊ የምግብ ችግር ላይ መሆኗን ትናንት ሀሙስ ያወጀች ሲሆን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዕርዳታ እንዲያደርግላት ተማጽናለች፡፡

ቻድ የዕርዳታ ተማጽኖዋን ያቀረበችው ሞስኮ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ ስላለው የእህል አቅርቦት ጉዳይ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና የሩሲያ ፕሬዚዳንት በዛሬው ዕለት በሚያካሂዱት ውይይት ዋዜማ መሆኑን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የቻድ ወታደራዊ አገዛዝ ባወጣው አዋጅ የሚመለከታቸው የሀገር ውስጥ አካላት እና ዓለም አቀፍ አጋሮቻችን እንዲረዱን እንማጸናለን ብሏል፡፡

ከአጠቃላዩ የቻድ ህዝብ አንድ ሦስተኛው ማለትም አምስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህዝብ በዚህ ዓመት ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠንቅቋል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ወረራ እና በማስከተልም ምዕራባውያን ሀገሮች በሞስኮ ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች ሁለቱ ሀገሮች የሚልኩትን የስንዴ አቅርቦት ያስተጓጎለ ሲሆን በዓለም ዙሪያ የረሃብ ሥጋትን አቀጣጥሏል፡፡

ከዓለም የስንዴ አቅርቦት ወደሠላሳ ከመቶ የሚሆነውን ሲያቀርቡ የቆዩት ሩሲያ እና ዩክሬን ናቸው፡፡

ዛሬ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር የሆኑትን የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳልን ተቀብለው እንደሚያነጋግሩ የህብረቱ ሊቀ መንበር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

“የአፍሪካ ህብረቱ ሊቀ መንበር እና የሩሲያ ፕሬዚዳንት ፑቲን በእገዳው በተለይ የአፍሪካ ሀገሮችን እየተጎዱ እንደመሆኑ የእህል እና የማዳበሪያ ክምችቱ መለቀቅ ስለሚቻልበት መንገድ ይወያያሉ፡፡” ሲል መግለጫው ጨምሮ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG