በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኦሮምያ ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገለፀ


ፍኖተ ሰላም ከተማ
ፍኖተ ሰላም ከተማ

በፀጥታ ችግር ምክንያት ከኦሮምያ ክልል ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ መጀመሩን ሁለቱ ክልሎች ገልፀዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን እንዳስታወቀው አስተማማኝ ሰላም አለባቸው ወደተባሉ የኦሮምያ ክልል 13 ዞኖች በመጀመሪያው ዙር ከ500 በላይ አባዎራዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉን አስታውቋል፡፡

በኦሮምያ ክልል የቡሳ ጎኖፋ ኮሚሽን በበኩሉ ከቅርብ ጊዜው እንቅስቃሴ ባለፈ እስካሁን በተደረጉ ጥረቶች ከአማራ ክልልም ሆነ ከኦሮምያ ክልል ተፈናቅለው የነበሩ ከ240 ሸህ በላይ የሁለቱም ብሔረሰብ ተወላጆች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን አረጋግጧል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ሁለት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

ዘገባው የመስፍን አራጌ ነው።

ከኦሮምያ ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:02 0:00

XS
SM
MD
LG