በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ ውስጥ የተመድ ሰላም አስከባሪዎች ላይ ጥቃት ደረሰ


ፎቶ ፋይል፦ የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች
ፎቶ ፋይል፦ የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች

ሰሜናዊ ማሊ ውስጥ ሰላም አስከባሪዎችን ይዘው በአጀብ በሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ተጠርጣሪ አሸባሪዎች ጥቃት ማድረሳቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት አስታወቀ፡፡ አንድ ዮርዳኖሳዊ ሰላም አስከባሪ ሲገደል ሌሎች ሶስት ዮርዳኖሳውያን ሰላም አስከባሪዎች መቁሰላቸውንም ገልጧል፡፡

አጥቂዎቹ አቅርቦት ጭነው ይጓዙ በነበሩት ሰላም አስከባሪዎቹ ላይ ለአንድ ሰዓት ያህል በሮኬት ላውንቸር አና በአነስተኛ የጦር መሳሪያዎችም ጭምር ያለማቋረጥ የተኮሱባቸው መሆኑ የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ተናግረዋል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ጥቃቱን አጥብቀው አውግዘዋል፡፡ ለሰላም አእስከባሪዎቹ ቤተሰቦች እና ለዮርዳኖስ መንግሥት የሀዘን መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ማሊ በሚገኘው የድርጅቱ የሰላም አስከባሪ ተልእኮ መሰረት ኪዳል በሚባለው የሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ በሰላም አስከባሪዎች ላይ እንዲህ ያለ ጥቃት ሲደርስ ይህ ስድስተኛ ጊዜ መሆኑን ዱጃሪች ገልጸዋል፡፡

የጸጥታ ምክር ቤቱም ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን አውግዞ የማሊ መንግሥት ምርመራ አካሂዶ ተጠያቂዎቹን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቋል፡፡ ሰላም አስከባሪዎችን ዒላማ በማድረግ የሚሰነዘር ጥቃት በጦር ወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ሲልም አሳስቧል፡፡

XS
SM
MD
LG