በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"እርምጃ የወሰድነው በሕገ ወጦች ላይ ነው" - የአማራ ክልል መንግሥት


"እርምጃ የወሰድነው በሕገ ወጦች ላይ ነው" - የአማራ ክልል መንግሥት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:11 0:00

"እርምጃ የወሰድነው በሕገ ወጦች ላይ ነው" - የአማራ ክልል መንግሥት

ከሦስት ሳምንታት በፊት የጀመረው እና “የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ” ብሎ የሰየመው እርምጃ እንደሚቀጥል የገለፀው የአማራ ክልል መንግሥት ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርብበትን ትችትና ውንጀላዎች አጣጥሏል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ከፋኖ ጋር በተያያዘ የሚሰነዘሩ ትችቶችን መሰረተ ቢስ ናቸው ብለዋል፡፡ መንግሥት አሁንም ከፋኖ ጋር እየዋለ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ በቁጥጥር ስር እያዋልን ያለነው ፋኖዎችን ሳይሆን በስማቸው የሚነግዱትን ህገወጦች ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

የአትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተከታታይ ባወጧቸው መግለጫዎች “የጅምላ እስር” ሲሉ የገለፁትን የክልሉን መንግሥት እርምጃ አውግዘዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትም በአማራ ክልልና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የታሰሩ ጋዜጠⶉች እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

ዘገባው የአስቴር ምስጋናው ነው።

XS
SM
MD
LG