የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች የኑሮ ውድነት ከአቅማቸው በላይ መሆኑን በመግለፅ፣ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ።
በአብዛኛው በውጭ ምንዛሪ የሚገዙ ሩዝ እና ፓስታ የመሳሰሉ የምግብ ሸቀጦችን ተመጋቢ የሚበዛበት ክልል በመሆኑ፤ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱና የጥቁር ገበያ ዋጋው መናር የክልሉን ሕዝብ ለከፍተኛ ዋጋ ውድነት ተጋላጭ እንዳደረገው ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
የክልሉ ካቢኔ በክልሉ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት ለመከላከል በአጭር እና በመካከለኛ ጊዜ የሚተገበሩ አራት ዋና ዋና ውሳኔዎችን መወሰኑን ያስታወቀ ሲሆን ከውሳኔዎቹም መካከል አንዳንድ በጀቶችን በማጠፍ ለመንግሥት ሠራተኞች እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ድጎማ ማድረግ የሚል ይገኝበታል።
ዘገባው የአዲስ ቸኮል ነው።