- እጅ ከሰጡት ውስጥ የታሰሩት ብዙ ናቸው ብሏል
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት በመተከል ዞን ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ከ1200 በላይ የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጉህዴን/ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጅ ሰጥተው ከኅብረተሰቡ ጋር መቀላቀላቸውን አስታወቀ።
የክልሉ ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ እንደገለፀው፣ ያለጸጥታ ኃይል እጀባ የመጓጓዣ አገልግሎት በዞኑ ውስጥ መጀመሩንም አስታውቋል።
በሌላ በኩል ጉህዴን፣
"በሰላማዊ መንገድ እጅ ሰጥተው የገቡ 110 ታጣቂዎች ታስረውብኛል፤ የመንግሥት ኃይሎች ተኩስ እየከፈቱ ነው እንዲሁም የነዋሪዎችን ቤት እያቃጠሉ ነው" ሲል አቤቱታ ያሰማ ሲሆን የሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ
"ይህ ፍረጃ ተገቢነት የሌለው ነው" ሲሉ አስተባብለዋል።
ዘገባው የናኮር መልካ ነው።